በ2014 በጀት ሩብ ዓመት በኦሮሚያ ክልል በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች ከ400 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ

በኦሮሚያ ክልል በ2014 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 1 ሺህ 66 የትራፊክ አደጋዎች መከሰታቸውን በኦሮሚያ ትራፊክ ትምህርት እና ግንዛቤ ምክትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር በላቸው ትኪ ገልፀዋ፡፡

በተከሰተው አደጋ 411 ሞት፣ 342 ከባድ እና 313 ቀላል የአካል ጉዳት ተመዝግቧል፡፡ እንዲሁም 422 የንብረት ውድመት የደረሰ ሲሆን ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ83 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚገመት ተገልፆል፡፡

ከአደጋዎቹ ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበው በምስራቅ አርሲ፣ ምእራብ ባሌ፣ ምስራቅ ሀረርጌ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ ወለጋ ዞኖች እና አዳማ፣ ዱከም፣ ቡራዩ፣ ሰበታ እና ሱሉልታ ከተሞች ናቸው፡፡

88 በመቶ የተከሰተው አደጋ የደረሰው በወንድ አሽከርካሪዎች ሲሆን፤ እንዲሁም 75 በመቶ የሚሆነው አደጋ በቀኑ ክፍለ ጊዜ የደረሰ ሲሆን 25 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በሌሊቱ ያጋጠሙ መሆናቸውን ለብስራት ሬዲዮ ገልጸዋል።

ያለ እረፍት ማሸከርከር፣ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከፍጥነት ወሰነ በላይ ማሽከርከር እና የአሸከርካሪዎች ጥንቃቄ ጉድለት የአደጋዎቹ መንስኤዎች ስለመሆናቸዉ ኮማንደር በላቸው ትኪ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe