ሃይንከን ኢትዮጵያ ፕሮጀክቱን እንዲተገብርለት ሃላፊነት ከሰጠው ማህበረ ህይወት ፎር ሶሻል ዴቭሎፕመንት (ኤምኤስዲ) ከተሰኘ መንግሰታዊ ያልሆነ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር በከብት ማድለብና ምግብ ማቀነባበር የስራ ዘርፍ ላይ ያተኮረውን ፕሮጀክቱን ለተጠቃሚዎቹ በዛሬው እለት በይፋ አስረከበ። ፕሮጀክቱ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በቂሊንጦ አካባቢ የሚገኙና ዝቅተኛ ኑሮ የሚኖሩቤተሰቦችን ተጠቃሚ ያደረግ ነው፡፡
አቶ ፍቃዱ በሻህ የሄኒከን ኢትዮጵያ የሰስተነብሊቲ የውጭና የመንግሥት ጉዳዮች ኃላፊ በቂሊንጦና በኮዬ ፈጪ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ወገኖች ለመደገፍ 5 ኘሮጀክቶች ተግባራዊ መሆናቸውን በጠቅላላው በ33 ሚሊዮን ብር ወጪ የተተገበረው ይህ ፕሮጀክት 75 አባወራዎችን ማለትም 30 በቂሊንጦ እና 45 በኮዬ ፈጬ የሚገኙ ነዋሪዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል። ተጠቃሚዎቹ በእንስሳት ማድለብ፣ በወተት ከብት ማርባት፣ በከብት ማደለብ፣ በዶሮ እርባታ እና በባልትና ንግድ የሚሰማሩ ሲሆን፤ በአካባቢው የምግብ ዋስትና እና ኢኮኖሚ ለመፍጠር የሚያግዝ እንሆነ ተናግረዋል።
ሃይንከን ኢትዮጵያ በዚህ ፕሮጀክት ዋና ግብ ያደረገው የችግረኛ ቤተሰቦችን የቤተሰብ ገቢን ማሳደግ ነው። ሃይንከን ለተጠቃሚዎቹ ደረጃውን የጠበቀ የስራ ቦታ (ሼድ) ከመገንባቱ በተጨማሪ የሚረቡትን ከብቶች፣ መኖ፣ እንቁላል ጣይ ዶሮዎች፣ የእንስሳት ህክምና ድጋፍ እና በምግብ ማቀናበር ለተሰማሩት ደግሞ ጤፍ፣ ገብስ፣ ስንዴ፣ በርበሬ፣ ሽሮና ምጣዶችና ሌሎች ለስራው የሚሆኑ ግብአቶችን ሰጥቷል፡፡ የእድሉ ተጠቃሚዎች በአብዛኛው የቤተሰብ ሃላፊ የሆኑ እናቶች ሲሆኑ ወደ ስራው ከመግባትቸው በፊት ከስራው ጋር የተያያዙ ስልጠናዎችም ተሰጥቷቸዋል፡፡
ይህ ፕሮጀክት የገቢ ማስገኛ አቅሞችን ከማሳደግ ባለፈ የሰራ ዕድል ፈጠራ እና ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር ታልሞ የተነደፈ በመሆኑ ሃይንከን ለዘላቂ የማህበረሰብ ልማት ያለውን ተከታታይ ድጋፍም ያሳያል።
ተጠቃሚዎቹን ለመምረጥና የስራ ፍላጎታቸውን ለመለየት ከሃይንከን፣ ኤምኤስዲ፣ ከማህበረሰብ አባላት እና ከመንግስት አካላት የተዋቀረ ቡድን በጋራ በመሆን የማጣራትና የስራ ፍላጎት ዳሰሳ አካቢዷል፡፡ በምርጫ ሂደቱ ለሴቶች በተለይም በሴቶች ለሚመሩ ቤተሰቦች እና አካል ጉዳተኞች ያላቸውን ተጋላጭነት በመገንዘብ ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
የሄኒከን ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ባርት ዲ ኬኒንክ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ከከብት እርባታ ጋር የተገናኙ ፕሮጀክቶች በከተማ ጠቀስ አካባቢዎችና በከተማ ባሉ ማህበረሰቦች ላይ ስለሚኖረው የጎላ ሚና በአፅንዖት ተናግረዋል። የፕሮጀክቱን የረዥም ጊዜ ስኬት ለማረጋገጥ በቴክኒክ ስልጠና፣ በገበያ ትስስር እና በዘላቂ የአመራር ዘዴዎች ሃይንከን የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።





