ፍትሕ ሚኒስቴር ለኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰሞኑን በፃፈው ደብዳቤ የውጭ ሀገር ገንዘብ ይዘው የተገኙ ሰዎች ላይ ይቀርብ የነበረውንየወንጀል ተጠያቂነት ቀሪ እንዲሆን አቅጣጫ መቀመጡን አስታወቀ፤
ሚኒስቴሩ በእጃቸው ላይ 100 ዶላርና ተመጣጣኝ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን ይዘው የሚገኙ ሰዎች ገንዘቡን በመውረስ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ሲደረግ የወንጀል ተጠያቂ ሆነው ክስ ይመሰረትባቸው የነበረውን ሂደት እንዲቀር ተደርጓል ይላል ደብዳቤው፡፡
ሚኒስትሩ በዚህ ሂደት ገንዘቡ የሚወረስባቸው ሰዎች ላይ የወንጀል ተጠያቂነቱ ከዚህ በኋላ እንዲቀር ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት የውጭ ሀገር ገንዘቦችን ሲመነዝሩ የተያዙና ጉዳያቸው በፍርድ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎችም ክሳቸው እንዲቋረጥ ይደረጋል ይላል፤
ከዚህ በፊት ከህገወጥ ምንዛሪ ጋር ተያያዘ በማስረጃ ተረጋግጦባቸው የተፈረደባቸው ግለሰቦችም በይቅርታ እንዲፈቱ እንዲደረግ አቅጣጫ መቀመጡ ታውቋል፤
በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ላይ በወንጀል ተጠያቂ የሚያደርገው ይህ ህገ ወጥ ድርጊት የወንጀል ተጠያቂነቱን ቀሪ እንዲሆን ፍትህ ሚኒስቴር ያደረገበትን ምክንያት በሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎች የተፈረመው ደብዳቤ አያብራራም፤

