በመዲናዋ በካይ የፍሳሽ ቆሻሻን ወደ ወንዝ የለቀቀው ድርጅት 800 ሺሕ ብር ተቀጣ

👉 ድርጅቱ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ደንብ መተላለፍ 400 ሺሕ ብር ተቀጥቶ ነበር

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአቃቂ ቃልቲ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ሥሙ ቦቼ ሰፈር አካባቢ በኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ ስር አዋሽ የቆዳ ፋብሪካ የተሰኘ ድርጅት፤ ከፋብሪካው የመነጨ በካይ የፍሳሽ ቆሻሻን ወደ ወንዝ በመልቀቁ 800 ሺሕ ብር መቀጣቱን አስታውቋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 06 ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ደሳለኝ ሌንጮ እንደገለፁት፤ ድርጅቱ ከዚህ በፊት ተመሳሳይ የደንብ መተላለፍ ፈፅሞ 400 ሺሕ ብር ተቀጥቶ ነበር፡፡

ዳግመኛም ከጥፋቱ ሳይታረም ለሁለተኛ ጊዜ ያመነጨውን በካይ ፈሳሽ ቆሻሻውን በድጋሚ ጨለማን ተገን አድርጎ ወደ ወንዝ ሲለቅ በደረሰ የማህበረሰብ ጥቆማ መሠረት በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ በተቀመጠው የቅጣት አወሳሰድ እርምጃ በተደጋጋሚ ጥፋት አጥፊ ሆኖ 800 ሺሕ ብር መቀጣቱ ተገልጿል።

ኃላፊው አክለውም ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት መድቦ የወንዝ ዳርቻ የልማት ሥራዎችን እየሰራ ባለበት ወቅት እንደዚህ አይነት ተግባር መፈፀም ተገቢ አለመሆኑን ገልጸው፤ ሌሎች ተቋማት ሆኑ ግለሰቦች ከዚህ እርምጃ መማር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe