በሰሜን አሜሪካ ግረንድ አፍሪካ ረን ለ7ኛ ጊዜ በመጪወ ጥቅምት እንደሚካሄድ ተገለጸ፤ ግራንድ አፍሪካ ረን’ በሚል ተቀራራቢ ስያሜ ሩጫ ሊያዘጋጁ ያሰቡ አካላት ስሙን ከተጠቀሙ በህግ እንደሚጠየቁ አዘጋጆቹ አስታወቁ።
በሰሜን አሜሪካ ግረንድ አፍሪካ ረን ለ7ኛ ጊዜ እንደሚካሄድ መግለጫ ሲሰጥ ‘ግራንድ አፍሪካ ረን ‘በሚል ተቀራራቢ ስያሜ ሩጫ ሊያዘጋጁ ያሰቡ አካላት ስሙን መጠቀም እንደማይችሉና ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ተጠይቋል ።
ስሙን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመጠቀም ህጋዊ ምዝገባ እና ፍቃድ ያለው – ግራንድ አፍሪካን ረንን የሚያዘጋጀው እና ተቀማጭነቱን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው – የኖቫ ኮኔኽንስ ተቋም ብቻ መሆኑን በመግለጫው ተነግሯል።
ስሙን ለመጠቀም ያሰቡት ከኛ መግለጫ ተቃራኒ ሆነው ከሄዱ በሕግ ለመጠየቅ እንደሚገደዱ አዘጋጆቹ ለባላገሩ ስፖርት አብራርተዋል ።
ባላገሩ ስፖርት

