በሽረ እንደስላሴ ከተማ 250 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ፡፡ እነዚሁ ሰዎች በ18 ሺሻ ቤቶች ነው በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባለው፡፡
የሽረ እንደስላሴ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት በከተማው የተለያዩ አካባቢዎች ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ የሺሻ እቃዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉንም አስታውቋል፡፡
ፖሊስ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ አለባቸው ተብለው በተለዩ ስፍራዎች ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ 152 የሺሻ እቃዎችን መያዙን ገልጻል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ 18 የሺሻ ቤት ባለቤቶች እና 250 ተጠቃሚዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል፡፡
የሺሻ ቤት ባለቤቶች ጉዳይ በመደበኛ ፍርድ ቤት የተጠቃሚዎች ጉዳይ ደግሞ በማህበራዊ ፍርድ ቤት እየታየ መሆኑንም ፖሊስ ገልጻል፡፡//

