በበርካታ ፖሊስ ጣቢያዎች ለተጠርጣሪዎች ምግብ እንደማይቀርብና የበጀት እጥረት እንዳለ ኢሰመኮ አሰታወቀ

የኢሰመኮ የ11 ወራት ሪፖርት ለፓርላማ ዛሬ ቀርቧል።የተነሱት ዋና ዋና ነጥቦች:-

📌 በበርካታ ፖሊስ ጣቢያዎች ለተጠርጣሪዎች ምግብ እንደማይቀርብ፣ የምግብ ጥራትና የበጀት እጥረት እንዳለ፣ የቦታ መጨናነቅ እንዲሁም ሕፃናት ከአዋቂዎች ጋር ተደባልቀው መታሰራቸው ተረጋግጧል።

📌 በደቡብ ኢትዮጵያ፣ ኦሮሚያ፣ አማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የባንክ ብድር፣ የሊዝ፣ የማዳበሪያ እና የጤና መድህን ዕዳዎችን ምክንያት በማድረግ ያለ ፍርድ ቤት ውሳኔ የዘፈቀደ እስራቶች እየተፈጸሙ ነው።

📌 በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና አፋር ክልሎች በ”ወቅታዊ ጉዳይ” ታስረው የነበሩ 2,143 ሰዎች በኮሚሽኑ ጥረት ከእስር እንዲለቀቁ ተደርጓል።

📌 ኮሚሽኑ 1,510 አቤቱታዎችን ተቀብሎ ለ1,022ቱ እልባት የሰጠ ሲሆን፣ 59 የአደጋ ጊዜ ክትትልና ምርመራዎችን አከናውኗል።

📌 በግንባታ፣ በእርሻ እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች (አዳማና ሐዋሳ) የሠራተኞች መብት ቁጥጥር አነስተኛ ነው። የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ለመጠበቅ የካምፓላ ስምምነት ሕግ እንዲጸድቅና ካሳ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

Source(Tikvah)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe