በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ አራት ቢሊዮን ብር በታክስ ክርክር ለግብር ከፋይ መወሰኑን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ሚኒስቴሩ በታክስ ክርክር የሚሸንፍበት ጊዜ መኖሩን ገልጾ፤በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 3.9 ቢሊዮን ብር ለግብር ከፋዩ የተወሰነ ነው ብሏል፡፡
በተመሳሳይ በጀት ዓመት ወደ 2ሺ የሚደርሱ ግብር ከፋዮች ከስራ መውጣታቸወን የገለጸው ሚኒስቴሩ፤በአንጻሩ 13ሺ የሚደርሱ አዳዲስ ግብር ከፋይ ድርጅቶች ወደ ታክስ ስርዓት መግባታቸውን ገልጻል፡፡

