በኖቫ ኮኔክሽን አዘጋጅነት በዋሽንግተን ዲሲ ለ7ኛ ጊዜ የሚደረገው ውድድር እና ዕውቅና በውጭ የሚኖሩ ዜጎችን በማቀራረብ ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን ተነረገ

“አብሮነት መሻል ነው”በሚል የሚደረገው ታላቁ የአፍሪካ ሩጫ በአሜሪካ ምዝገባ ተጀመረ። ውድድሩ በመጪው ጥቅምት ወር ላይ ይደረጋል ተብሏል።
በውጭ ዓለም የሚኖሩ ዜጎችን የሚያቀራርብ እና ለሀገራቸው የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለውለታዎች እውቅና የሚያገኙበት መርሐ ግብር ጥቅምት ወር ላይ እንደሚካሄድ አዘጋጁ ኖቫ ኮኔክሽን አሳውቋል።
በዋሽንግተን ዲሲ ለ7ኛ ጊዜ የሚደረገውን ውድድር እና ዕውቅና በተመለከተ  የማስጀመርያ መርሐ ግብር ሲካሄድ፤ በመድረኩ አትሌቶች እና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል።
ጅማሮውን በ2012 ዓ.ም ያደረገው ታላቁ የአፍሪካ ሩጫ፤ በአሜሪካ የአዋቂዎች 5 ኪሎ ሜትር እና የህጻናት አንድ ኪሎ ሜትር ውድድር የሚደረግበትም ይሆናል።
ለሁለት ቀን በሚቆየው መድረክ ጥቅምት አንድ ቀን በዋሽንግተን ዲሲ የ5 ኪሎ ሜትሩ ውድድር ሲደረግ፤ ጥቅምት ሁለት ደግሞ የሀገር ባለውለታዎች ዕውቅና የሚሰጡበት እንደሆነም ይፋ ተደርጓል።
የኖቫ ኮኔክሽን መስራች እና ስራ አስፈጻሚ ጋሻው አብዛ (ዶ/ር)፥ በዲሲ የሚደረገው ዓመታዊ ውድድር በውጭ የሚኖሩ ዜጎችን በማቀራረብ ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን ተናግረዋል።
የዘንድሮ የአፍሪካ ታላቁ ሩጫና የአፍሪካውያን ተፅኖ ፈጣሪ የሽልማት መርሃግብር “አብሮነት መሻል ነው” በሚል መሪቃል ይከናወናል ተብሏል።
የኖቫ ኮኔክሽንስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶ/ር ጋሻው አቤዛ፤ ይህ መድረክ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች እንዲሁም አፍሪካዊያን በሰፊው የሚሳተፉበት ነው ብለዋል።
ዶ/ር ጋሻው “ዲያስፖራውን አፍሪካውያን ማህበረሰብ ወደ አንድ የሚሰበስበውን ይህን ዝግጅት ማዘጋጀታችን ለእኛ ትልቅ ክብርና ኩራት ነው” ብለዋል።
ሆኖም የዚህ አመት የአፍሪካ ታላቁ ሩጫ በፈረንጆቹ ኦከክቶበር 11/2025 እንደሚከናወንና የአፍሪካውያን ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሽልማት መድረክ ደግሞ በጥቅምት 12 ቀን 2025 እንደሚደረግ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
አንድነት፣ ፍቅር ፣ መተሳሰብና መረዳዳት በጉልህ በሚታይበት በዚህ አዝናኝ ሩጫ እንዲሁም የእግር ጉዞ ዝግጅቱን በርካታ ታዋቂ አጋሮችና ስፖንሰሮች ድጋፋቸውን አረጋግጠዋል።
የውድድሩ ምዝገባ ዛሬ በይፋ መጀመሩም በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል።
ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣  ቴዲ አፍሮ፤ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ሙላቱ አስታጥቄ፣ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ እና አስቴር አወቀን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ግለሰቦች በተጽእኖ ፈጣሪ ሽልማት በኩል እውቅና የተሰጣቸው ናቸው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe