በአማራ ክልል የተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ በመከላከያ ሰራዊት ተበተነ

በአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ወኃ ከተማ የሚገኙ ተማሪዎች ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ። የዓይን ምስክሮች ለዶይቸ ቬለ እንደተናገሩት፦ ተማሪዎች ሰልፍ ያካሄዱት በአግባቡ ትምህርት ሳይከታተሉ ፈተና ውሰዱ በመባላቸው ነው። «ኹሉም ትምህርት ቤት ከተማው ላይ ያለ፤ ምክንያቱ ምንድን ነው፤ እስካሁን በተሟላ መንገድ ተማሪው ትምህርት ገበታው ላይ አልተቀመጠም።

ተጨማሪ የትምህርት ጊዜ ሠሌዳ ተሰጥቶ ሳይማሩ ቀጥታ ወደ ፈተና ነው የገቡት። እና ሳያስተምሩን ከርመው እንዴት ቀጥታ መጥተው ወደፈተና ያስገቡናል ነው ዋናው ምክንያት። ሳንማር እንዴት እንፈተናል፤ ሳናውቅ እንዴት እንፈተናለን ነው።»የማካካሻ ትምህርት ሳይሰጠን እንዴት እንፈተናለን የሚሉት ተማሪዎች ሰልፍ፣ በመከላከያ ሠራዊት መበተኑን እነዚሁ የዓይን ምስክሮች ለባሕር ዳሩ ዘጋቢያችን ነግረውታል።

የዓይን እማኞች ይህን ይበሉ እንጂ፤ የምእራብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ የትምህርት ቡድን መሪ አቶ ሥዩም ታደሰ ግን ተማሪዎቹ ሰልፍ የወጡት የማካካሻ ትምህርት ሳይማሩ ቀርተው ሳይሆን ተፈናቅለው የነበሩ መምህራን ወደ ትምህርት ቤቱ ዘግይተው መምጣታቸውን በመቃወም ነው ብለዋል። «ፈተና ተቀመጥን በሚል አይደለም። ወጥተው የነበሩ መምህራን አኹን ባለቀ ሰአት መጥተው እነሱ አያስተምሩንም በሚል ነው እንጂ ማካካሻ ምናምን የሚል ነገር አይደለም።

አስፈላጊ ዝግጅት ተደርጎ፤ ትምህርታቸው በበቂ ኹኔታ መሸፈን የሚገባቸው ነገሮች ተሸፍነዋል። ተማሪው እንዲሰበሰብ ተደርጎ፤ ውይይት ተካሂዶ ነው የተበተነው እንጂ መከላከያ ምናምን አልበተነውም።»በአማራ ክልል በምዕራብ እና ጎንደር ዞኖች በተፈጠረው ግጭት በርካታ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውንና ትምህርትም መቋረጡን ዶይቸ ቬለ ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe