በአሜሪካና በኢራን መካከል የተደረሰው የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት በመላው ዓለም ከፍተኛ ተስፋን እየፈጠረ ይገኛል

ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው ፍጥጫ ወደ ከፋ ቀውስ እንዳያመራ ከማድረጉም ባለፈ፣ ለዓለም የነዳጅ አቅርቦት ቁልፍ የሆነው የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ዳግም እንዲከፈት መንገድ የሚከፍት በመሆኑ ለዓለም ኢኮኖሚ ትልቅ እፎይታ ተፈጥሯል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እርምጃውን አዎንታዊ ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ ስምምነቱ ለዘላቂ ሰላም መንገድ የሚከፍትና በግጭቱ ሳቢያ የሚደርሰውን ሰብዓዊ ስቃይ ለመቀነስ ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የቻይና፣ የሩሲያ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የጀርመን፣ የፈረንሳይና የጃፓን መሪዎች በበኩላቸው ግጭቱን በዲፕሎማሲ ለመፍታት የተያዘው አቅጣጫ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተለይም በቀጣዩ ዓርብ በፓኪስታን ኢስላማባድ የሚጀመረው የሰላም ውይይት ለመካከለኛው ምስራቅ መረጋጋት ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡
በሌላ በኩል እስራኤል የአሜሪካን ውሳኔ እንደምትደግፍ ብትገልጽም፣ የተኩስ አቁሙ በሊባኖስ በኩል ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደማያካትት አስታውቃለች፡፡
ይህ መረጃ እየተጠናቀረ ባለበት ሰዓት፣ በዓለም የነዳጅ ገበያ ላይ መጠነኛ የዋጋ ቅናሽ መታየት መጀመሩን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ጠቁመዋል፡፡
አብዛኞቹ የዓለም ሀገራት ፓኪስታን ለተኩስ አቁሙ መሳካት ላበረከተችው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ዕውቅና የሰጡ ሲሆን፣ አሁን የዓለም ትኩረት በኢስላማባድ በሚደረገው የታሪክ ስምምነት ላይ ማረፉን የአልጄዚራ ዘገባ ያመላክታል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe