በአሜሪካን የሚኖር ኢትዮጽያዊ የ140ሚ ሊዮን ብር ሎተሪ አሸናፊ መሆኑ ተገለጸ

በአሜሪካን ሀገር ሜሪላንድ አካባቢ ነዋሪነቱ የሆነ አንድ ኢትዮጽያዊ የአንድ ሚሊዮን ዶላር ሎተሪ እንደ ወጣለት ተነግሯል፡፡

ነዋሪነቱ በሜሪላንድ አካባቢ የሆነው ኢትዮጽያዊ ስደተኛ ጎልድ ረሽ 777 በተባለው ሎተሪ አማካኝነት የአንድ ሚሊዮን ዶላር እድለኛ መሆኑ ታውቋል፡፡ ስሙን ለመገናኛ ብዙሃን መግለጽ ያልፈለገው ይሄው ኢትዮጽያዊ ሜሪላንድ በሚገኘው የሎተሪ አስተዳደር ትላንት በመሄድ የአንድ ሚሊዮን ዶላሩን ሽልማት አሸናፊነቱን እንዳሳወቀም ተገልጻል፡፡

ግለሰቡ ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ ይህንን ሎተሪ ይቆርጥ እንደነበርም መግለጹ ተሰምቷል፡፡ በ20 ዶላር የቆረጠው ሎተሪ በህይወቱ አስቦት የማያውቀውን ገንዘብ እንዳስገኘለት ገልጻል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe