በአምስት አመት ውስጥ አንድም ተማሪ ለዩኒቨርስቲ ያላሳለፈው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አለ ተባለ

 በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳዉሮ ዞን፣ ማሪ-ማንሳ ወረዳ ውስጥ ካሉ ከሦስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የአሰሊ-መንድዳ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ካስፈተናቸው ተማሪዎች ውስጥ አንድም ተማሪ እንዳላለፈ ታውቋል።
የትምህርት ቤቱ አመራሮች እና ወላጆች ለመሠረት ሚድያ እንደተናገሩት የተማሪዎች የመማሪያ ክፍሎች በቅጡ አለመዘጋጀት፣ የመማሪያ መጽሐፍት አለመኖር፣ የተማሪ መቀመጫ እና ወንበር እጥረት፣ የቤተ-መጻህፍት አለመኖር፣ ትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ ለተማሪ በሚመጥን መልኩ አለመሥራቱ እና ሌሎች ምክንያቶች ለዝቅተኛው ውጤት ምክንያት ሆነዋል ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ እስካሁን ድረስ የኢኮኖሚክስ ትምህርት የሚያስተምር መምህር ካለመኖሩና ካለመመደቡ የተነሳ ተማሪዎች የትምህርት ዓይነቱን ሳይማሩ ፈተና እንዲፈተኑ እየተደረጉ እንደሆነ ታውቋል።
የICT (ወይም የኮምፒውተር) ትምህርት በቲዎሪም ሆነ በተግባር እስካሁን እየተማሩ አለመሆናቸው በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ተብሏል።
ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል ብናቀርብም እስካሁን ድረስ ምላሽ ሊሰጥ ባለመቻሉ ተማሪና ትምህርት ቤቱ ከፍተኛ ችግር ዉስጥ ወድቋል ብለው ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe