የአርባምንጭ ከተማ ከሙዝ ዱቄት በተዘጋጀ እንጀራ እና ዳቦ የከተማዋውን ህዝብ መመገብ መጀመሩ ተሰማ፡፡
በኢትዮጽያ ከፍተኛ የሙዝ ምርት ካለባቸው ቦታዎች አንዷ የሆነችው አርባምንጭ ከተማ የሙዝ ፍሬን ወደ ዱቄትነት በመለወጥ ነዋሪዎቿ እንጀራ፡ዳቦ እና ገንፎ እንዲያዘጋጁ ማድረግ መጀመሯ ተሰምቷል፡፡
የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የሰሩትን ጥናታዊ ጹሑፍ መነሻ በማድረግ የሙዝ ፍሬን ወደ ዱቄትነት ለውጦ ለምግብነት ማዋል መቻሉን ዩኒቨርሲቲው ይፋ አድርጓል፡፡
በኢትዮጽያ በዚህ ስዓት ከጤፍ ብቻ የተዘጋጀ እንጀራ መመገብ ለብዙዎች የማይቻል ሆኗል፡፡ ይህን ተከትሎም ባለፈው ሰሞን ካሳቫ የተባለው ስር ከእንጀራ ዱቄት ጋር ተቀላቅሎ ለምግብነት መዋል እንደሚችል በምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ፍቃድ ማግኘቱ ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ እንጀራን ከሙዝ ዱቂት ማዘጋጀት እንደሚቻል በጥናት ተረጋግጦ ለምግብነት መዋል መጀሩ ተሰምቷል፡፡
እስካሁን ባለው ሂደት የሙዝ ዱቄት በተለያዩ የምግብ አይነቶች እየጠዘጋጀ ጥቅም ላይ መዋል የጀመረው በአርባምንጭ ከተማ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥም ወደ አዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች ይዳረሳል ተብሏል፡፡
ይሔው የሙዝ ዱቄት ታሽጎ ከ6 ወር እስከ 1ዓመት ድረስ የመቆት ሁኔታ እንዳለውም ተነግሯል፡፡
ግኙቱ በአካባቢው ያለውን የሙዝ ምርት ብክነትን ይታደጋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡
ምርቱ የኢትዮጽያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን መስፈርቶችን አሟልቶ ለገበያ ስለመቅረቡ ማወቅ ተችሏል፡፡

