በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብዙዎችን ያስደነገጠ አሳዛኝ ክስተት መፈጠሩ ተሰማ፡፡
በዩኒቨርሲቲው ጫሞ ካምፓስ ውስጥ ትላንት ረፋድ ላይ አንድ ተማሪ በዶርም ውስጥ በስለት ተወግቶ ህይወቱ ማለፉ ተነግሯል፡፡
ናትናኤል ፀጉ አሰፋ የተባለው የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት የሳይኮሎጂ ተማሪ በዶርም ውስጥ መገደሉን ዩኒቨርሲቲው ይፋ አድርጓል፡፡
ተማሪው የተገደለው በተፈጠረ የግል ጸብ ምክኒያት በስለት እንደሆነም ተሰምቷል፡፡
ሁኔታውን ተከትሎም ተማሪዎች ስጋት ውስጥ መውደቃቸውንና ደህንነታቸው እንዲረጋገጥላቸውም በመጠየቅ ላይ እንደሆኑ ተነግረዋል፡፡
ጥቃት አድራሹ የዚያው የዩኒቨርሲቲው ተማሪ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤በአሁኑ ስዓትም በቁጥጥስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ እንሆነ ዩኒቨርሲቲው ይፋ አድርጓል፡፡
የጫሞ ካምፓስ ተማሪ የነበረው ተማሪ ናትናኤል ፀጉ ትላንት ጠዋት አካባቢ ነው በአስከፊ ሁኔታ መገደሉ የታወቀው፡፡
ዩኒቨርሲቲው የተማሪውን ህይወት ለማትረፍ ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም ሳይሳካ ቀርቷል ነው ያለው ባወጣው የሀዘን መግለጫ ላይ፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው የህግ ሂደቱን ተከታትሎ ውሳኔውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም ባወጣው መግለጫ ላይ አሳውቋል፡፡//

