በአርጀንቲና በማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነችው ሚካኤላ ይባኔዝ በቀጥታ ስርጭት ላይ ስልኳን ተዘርፋለች።
ከእንግዳዋ ጋር በቦነሳይረስ ጎዳናዎች እየተዟዟረች ቃለምልልስ ማድረግ እንደጀመረች ነው በሞተር ሲከተላቸው የነበረ ግለሰብ የመኪናውን መስታውት ሰብሮ ስልኳን ነጥቆ እግሬ አውጪኝ ያለው።
“ሚሊካ” በሚል ቅጽል ስሟ የምትታወቀውና በማህበራዊ ሚዲያዎች ከ3 ሚሊየን በላይ ተከታዮች ያሏት ሚካኤላ ይባኔዝ ስልኳን ስትዘረፍ ተከታዮቹ በቀጥታ ተከታትለውታል።

