በአዲስ አበባ አንድ ነፍሰ ጡር ሴትን ጨምሮ 18 ሰዎችን የጫነ ሚኒ ባስ ዋና መንገድ ስቶ ወደ ወንዝ መግባቱ ተሰማ፡፡ ከነፍሰ ጡሯ ሴት በተጨማሪ ወደ ትምህርት ቤት በመሄድ ላይ የነበሩ ተማሪዎችም በታክሲው ውስጥ እንደነበሩ ታውቋል፡፡
አደጋው ዛሬ ረፋድ ላይ በጉለሌ ክ/ለ ከተማ ወረዳ 7 ጌሾ ወንዝ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ነው የደረሰው፡፡ በአደጋውም የአካል ጉዳት ከመድረሱ ውጭ እስካሁን በህይወት ላይ ያጋጠመ ጉዳት አለመኖሩ ተነግሯል፡፡
የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ተጎጂዎቹን ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስባቸው በፍጥነት ወደ ህክምና ቦታ ማድረሱን አስታውቋል፡፡ የአደጋው መንስኤና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች በፖሊስ በኩል ማጣራት እየተደረገበት እንደሆነ ኮሚሽኑ ገልጻል፡፡

