በአዲስ አበባ ለፋሲካ በዓል አንድ ኪሎ ስጋ በ460 ብር ሊቀርብ ነው መባሉ አነጋጋሪ ሆኗል

በአዲስ አበባ ለፋሲካ በዓል አንድ ኪሎ ስጋ በ460 ብር ሊቀርብ ነው መባሉ ሲነገር፤በአንጻሩ በመዲናዋ ባሉ ቁርጥ ቤቶች አንድ ኪሎ ስጋ ከቫት በፊት 2ሺ800 ብር ይሸጣል፡፡

በአንድ ከተማ ውስጥ አንድ ኪሎ ስጋ ከ2ሺ300 ብር በላይ ልዩነት እንዳለው ተነግሯል፡፡ የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በዓሉን እንዲውሉ ታሳቢ በማድረግ ነው አንድ ኪሎ ስጋ ከ460 እስከ 520 ብር ድረስ አቀርባለሁ ያለው፡፡

በከተማዋ ባሉ 239 የህብረት ስራ ማህበራት ስጋ ቤቶች ለበዓሉ ከ460 ብር ጀምሮ አንድ ኪሎ ስጋ እንዲያቀርቡ መደረጉ ይፋ ሆኗል፡፡

ከወጣው ተመን ውጭ እንዳይሸጥም በኮሚሽኑ በኩል ክትትል ይደረጋል መባሉም ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የቆዳ እና ሌጦ ምርት በሚፈለገው መጠን ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም ተብሏል፡፡ የበሬ ቆዳ በኮንትሮባንድ ንግድ መውጣቱ በዘርፉ ላይ ችግር መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በኢትዮጽያ በዚህ ስዓት የቆዳና ሌጦ ሃብት እየጨመረ ቢሆንም በሚፈለገው ልክ ጥቅም ላይ እየዋለ እንዳልሆነ የቆዳ አምራች ኢንደስትሪዎች ይፋ እያደረጉ ነው፡፡ በዓመት ከበሬ፡ከበግ እና ከፍል እስከ 41 ሚሊየን ቆዳ ይገኛል የሚል ግምታዊ መረጃ እንዳለ ይነገራል፡፡ አንድ የቆዳ ፋብሪካ የቆዳ ምርትን ለማከናወን በአንድ ጊዜ ከ3ሺ በላይ የበግ ቆዳ እንዲሁም ከ2 መቶ በላይ የበሬ ቆዳ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

በሀገር ደረጃ ያለው የእንስሳት ሃብት ከፍተኛ ቢሆንም፤ቆዳና ሌጦው በአግባቡ ተሰብስቦ ወደ ኢንደስትሪዎች እንደማይደርስ የቆዳ አምራች ኢንደስትሪ ልማት ኢንስትቲዩት ገልጻል፡፡ለዚህ ደግሞ እንደ ምክኒያት በህብረተሰቡ ያለው ግንዛቤ አናሳ መሆን እና ምርቶችን መሰብሰቢያ በቂ ቦታ አለመኖር እንደሆኑም ተጠቅሷል፡፡

በአሁኑ ወቅት የበሬ ቆዳ እጥረት አለ የተባለ ሲሆን ይህም የሆነው በኮንትሮባንድ ንግድ በመውጣቱ ነው ተብሏል፡፡አብዛኛው የቆዳ ፋብሪካዎች ከ99 በመቶ በላይ ለምርት ሂደት የሚጠቀሙት የበሬ ቆዳን መሆኑም ተሰምቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe