በአዲስ አበባ የደንብ ጥሰት ከፈጸሙ 190ሺ አካላት ከ360 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ

በተያዘው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ የደንብ ጥሰት ከፈጸሙ 190ሺ አካላት ከ360 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ፡፡

ከሐምሌ 2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 18 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከ190ሺ በላይ የተለያዩ የደንብ ጥሰቶች መፈጸማቸውን የከተማ አስተዳደሬ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ የበጀት ዓመቱን የዕቅድ አፈጻጸም ባቀረበበት ወቅት 191ሺ128 የደንብ ጥሰቶች መፈጸማቸውን ገልጻል፡፡ 3ሺ854 ህገ-ወጥ ግንባት፡12 ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ፡38ሺ27 ህገ-ወጥ ንግድ፡12ሺ140 ህገ-ወጥየደረቅና የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ እና 122ሺ826 ህገ-ወጥ ማስታወቂያ ከተፈጸሙ ጥሰቶች ውስጥ ናቸው ተብሏል፡፡

በዚህም 3ሺ809 ድርጅቶችና 51ሺ591 ግለሰቦች በደንብ መተላለፍ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡

ከቅጣትና ከጨረታ ሽያጭ 397.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል የተባለ  ሲሆን፤ከደንብ ተላላፊዎች ደግሞ 366.6 ሚሊዮን ብር በላይ እንደተሰበሰብም የሪፖርት ዘገባ ያመላክታል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe