በአፋር ክልል የጨው ፋብሪካ ያቋቋሙ ባለሃብት ፋብሪካውን ዘግተው ጠፉ

ከ4 ዓመት በፊት በ300 ሚሊዮን ብር በአፋር ክልል የጨው ፋብሪካ ያቋቋሙ ባለሃብት ባልታወቀ ምክኒያት ፋብሪካውን ዘግተው ጠፍተውብኛል ሲል ክልሉ ገልጻል፡፡

በክልሉ አፍዴራ ሐይቅ አካባቢ ከ3 ዓመት በፊት ተመርቆ ስራ የጀመረው TTR አዮዳይዝድ ጨው ማምራቸ ፋብሪካን የከፈቱት ባለሃብት ናቸው ጠፍተዋል የተባለው፡፡

ፋብሪካው በስዓት 1ሺ350 ኩንታል በቀን ደግሞ እስከ 20ሺ ኪንታል አዮዳይዝድ ጨው ያመርታል ተብሎ ነበር፡፡

በ2013 ዓ.ም ፋብሪካውውን መርቀው ስራ መጀመሩን ያበሰሩትም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፡የወቅቱ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር እንዲሁም ሚኒስትር ድኤታዎች ነበሩ፡፡

300 ሚሊዮን ብር ወጥቶበት በቀን 20ሺ ኩንታል ጨው ያመርታል ተብሎ የነበረው ይሔው ፋብሪካ ከተዘጋ ሁለት ዓመት እንዳለፈው የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ገልጻል፡፡

የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ አይሻ ያሲን ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የማዕድንና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በገለጹበት ወቅት ነው ይህ የተሰማው፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በአፋር ክልል ተገኝቶ TTR ፋብሪካን ተመልክቷል፡፡

የቢሮው ሃላፊ ለቋሚ ኮሚቴው ፋብሪካው ስራ ያቆመበትን ምክኒያት ሲያስረዱም ባለቤቱ ባልታወቀ ምክኒያት ፋብሪካውን ዘግቶ በመጥፋቱ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የፋብሪካው ችግር ታይቶ ዳግም ስራ እንዲጀምር ቋሚ ኮሚቴው እገዛ እንዲያደርግ መጠየቁም ተሰምቷል፡፡

ቋሚ ኮሚቴውም በችግሩ ዙሪያ ውይይት ተደርጎ ፋብሪካው ማምረት እንዲጀምር ጥረት እንደሚያደርግ ገልጻል ተብሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe