በኢትዮ-ጅቡቲ መስመር በየዓመቱ እስከ 250ሺ ኢትዮጽያዊያን ከሀገር እንደሚሰደዱ ተሰማ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በየዓመቱ በኢትዮ-ጅቡቲ መስመር ከ150ሺ እስከ 250ሺ የሚደርሱ ኢትዮጽያዊያን እየተሰደዱ መሆኑን ለአሐዱ ሬዲዮ ገልጻል፡፡ ዜጎች በህገ-ወጥ መንገድ ሀገራቸውን ጥለው በመሰደዳቸው ለተለያዩ ሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች እየተጋለጡ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

የህዝብ ቁጥር መጨመርና በገጠሩ አካባቢ በቂ የእርሻ መሬት አለመኖር ለችግሩ መባባስ እንደ አንድ ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ስደት ላይ እያሉ በተፈጥሯዊ እና በሰው ሰራሽ ምክንያቶች ህይወታቸው የሚያልፍ ዜጎች ቁጥርም ቀላል እንዳልሆነ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

መንግስት ለስደት አመቼ በሆኑ ድንበሮች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርግም ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe