በኢትዮጵያ ትልቁ የቢራ አምራች የሆነው ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ፒየር-ኤማኑኤል ሜዳርድን አዲሱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርጎ በይፋ ሾሟል።
ሜዳርድ ይህን ከፍተኛ የአመራር ቦታ የሚረከቡት ከዚህ ቀደም የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ሄርቬ ሚልሃዴ ከካስቴል ግሩፕ በጡረታ ለመውጣት ፍላጎታቸውን ካሳወቁ በኋላ መሆኑ ተሰምቷል።
ፒየር-ኤማኑኤል ሜዳርድ በቢራ እና በመጠጥ ኢንዱስትሪው ውስጥ ከ25 ዓመታት ልምድ ያላቸዉ ሲሆን ከዚህ ቀደም በኮንጎ የካስቴል ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን በመጠጥ ዘርፉ ጉልህ ውጤቶችን አስመዝግበዋል።
ከአስር ዓመት በፊት ካስቴል ግሩፕን ከተቀላቀሉ በኋላ በኮትዲቯር ከፍተኛ የአመራር ቦታዎችን የያዙ ሲሆን በጋምቢያ እና ሴኔጋል የካስቴል ኩባንያዎች ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ማገልገላቸውን ቢጂአይ ኢትዮጵያ ለቁም ነገር ከላከው መግለጫ መረዳት ችለናል።
በኢትዮጵያ ትልቁ የቢራ አምራች የሆነው ቢጂአይ ኢትዮጵያ አዲስ ስራ አስፈፃሚ ሾመ

