የኢትዮጵያ አዲስ የቡና ልማት ፓኬጅ፦ በሄክታር 21 ኩንታል የማምረት ግብ ይፋ ሆነ፡፡
☕️ ኢትዮጵያ የቡና ምርታማነትን በአሁኑ ወቅት ካለው በሄክታር አማካይ 9 ኩንታል ወደ 21 ኩንታል ለማሳደግ አዲስ ሀገራዊ የቡና ልማት ፓኬጅ ይፋ አድርጋለች።
ኢትዮጵያ በዚህ ፓኬጅ ምን ታሳካለች?
🟠 በ1.15 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ዘመናዊ የአመራረት ሥርዓት ለመዘርጋት ያስችላታል፡፡
🟠 ምርታማነትን በሄክታር ከ130% በላይ ያሳድጋል፡፡
🟠 የቡና ወጪ ንግድ ዓመታዊ ገቢ ወደ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ የያዘችውን ግብ ያፋጥናል።
🟠 ተጨማሪ መሬት ሳያስፈልግ የነባር ማሳዎችን ምርታማነት ይጨምራል፡፡
🟠 እንደ ብራዚል እና ቬትናም ካሉ የዘርፉ ግዙፍ አምራች ሀገራት ጋር ያለውን የውጤታማነት ልዩነት ያጠብባል።
🟠 ከ6 ሚሊዮን በላይ የቡና አምራች አርሶ አደሮችን ገቢና የኑሮ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ያሻሽላል።
👉 አዲሱ አሰራር ምርጥ ዘር መጠቀምን፣ የተቀናጀ የአፈርና መስኖ አጠቃቀምን፣ የቡና ጥግግትና ግረዛን፣ ተገቢ ጥላና የተባይ መከላከልን እንዲሁም የተሻሻለ የምርት አሰባሰብና የዛፎች ዕድሳትን ያካተተ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።

