በኢትዮጽያ የኒውክሌር ሕክምናን ማስፋፋት አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ነው ተባለ

የኒውክሌር ህክምና በተለይ ለካንሰር በሽታ ህክምና ውጤታማነት የላቀ አስተዋጾ እንዳለው የህክምና ሰዎች ይገላጻሉ፡፡ ነገር ግን በኢትዮጽያ አገልግሎቱን የሚሰጡ ተቋማት ከሁለት እንደማይበልጡ የኒውክሌር ህክምና ስፔሻሊስቶች ሃኪሞች ገልጸዋል፡፡

ባለሙያዎቹ ህከምናው በኢትዮጽያ ገና በመዳህ ላይ እንደሚገኝ አንስተው፤በመንግስት የተሰጠው  ትኩረት ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት መግለጻቸውን ከስፑትኒክ ኢትዮጽያ ዘገባ ላይ ተመልክተናል፡፡

ዘርፉ የህክምና አስተዳደርን ከ30 እስከ 50 በመቶ የመቀየር አቅም እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ይህ ማለት የኒውክሌር ህክምና ከሦስት ታካሚዎች የአንዱን፤ከፍ ሲልም የግማሹን የህክምና አሰጣጥ መንገድ የመቀየር አቅም አለው እንደ ማለት ነው ብለዋል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe