ዘጠና በመቶ የሚሆነው ዓመታዊ የመንግስት በጀት የሚደገፈው ከጠቅላላው ግብር ከፋዮች ውስጥ አስር በመቶ በታች በሆኑ ጥቂት ግብር ከፋዮች ነው ተብሏል፡፡
ከምርታማነት አንጻርም አብዛኛው የአገሪቱ ምርት በጥቂት ኩባንያዎች እንደሚሸፈን ተነግሯል፡፡
የኢትዮጽያ የግል ዘርፍ አጠቃላይ አስተዋጾ የሚገለጸው በጥቂት ኩባንያዎች ብቻ እንደሆነም የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች መናገራቸውን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
ባለሙያዎቹ ሚድሮክ ለአገር በሚል በተዘጋጀ የፓናል ውይይት ላይ ኢትዮጽያ ውስጥ ካሉ ግብር ከፋዮች 90በመቶውን ታክስ የሚከፍሉት አስር በመቶ የሚሆኑት ታክስ ከፋዮች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ይህም የሚያሳየው የመንግስት ዓመታዊ በጀት የመደገፍ ጫና በጥቂት ድርጅት ጫንቃ ላይ ያለ መሆኑን ነው ብለዋል፡፡
የመንግስት ግብር በጥቂት ድርጅቶች ላይ ለመውደቁ እንደ ምክንያት ከሚጠቀሱት ውስጥ በታክስ ስርዓቱ ውስጥ ያሉት ጥቂት መሆናቸውና ያሉትም ቢሆኑ በሙሉ ታክስ የማይከፍሉበት ሁኔታ ስላለ ነው ብለዋል፡፡//
በ2017 በጀት ዓመት 40 የመንግስት ድርጅቶች ከሁለት ሪሊዮን ብር በላይ ገቢ አግኝተዋል ተባለ፡፡
ድርጅቶቹን በበላይነት የሚያስተዳድረው የኢትዮጽያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት የተጣራ 262.7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘት መቻሉን ገልጻል፡፡
ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ88 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተጠቁሟል፡፡ ትራንስፖርት 66.8 በመቶ፡የፋይናስ አገልግሎት 14.95 በመቶ፡የቴሌኮምና የኃይል ዘርፍ በጋራ 10.08 በመቶ ለተገኘው ገቢ ቀዳሚ ደርሻ አላቸው ተብሏል፡፡
ባለፈው ሳምንት የኢትዮጽያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በ2.5 ቢሊዮን ዶላር የማዳበሪያ ፋብሪካ ለማቋቋም ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር ስምምነት መፈራረሙ ይታወቃል፡፡

