በኮሎምቢያ 17 ተማሪዎች በአስደንጋጭ ሁኔታ ህይወታቸውን አጡ

በኮሎምቢያ 17 ተማሪዎች በአስደንጋጭ ሁኔታ ህይወታቸውን እንዳጡ ተሰማ፡፡

ከሞቱት 17 ተማሪዎች በተጨማሪ 20 የሚሆኑት ደግሞ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ተነግሯል፡፡ በኮሎምቢያ ትላንት እሁድ በተማሪዎች ባስ ላይ ባጋጠመ አደጋ ነው የ17ቱ ተማሪዎች ህይወት የጠፋው፡፡

ተማሪዎች በሰሜናዊ የሀገሪቱ ገጠራማ ስፍራ ለመዝናናት እየተጓዙ ባለበት ወቅት ነው ይህ አስከፉ የትራፊክ አደጋ ተከስቶ ለ17 ተማሪዎች ህይወት መጥፋት እና 20 ለሚሆኑት ደግሞ የመቁሰል ምክንያት የሆነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ተማሪዎቹ የምርቃ በዓል ቀናቸውን እያከበሩ ነበር ተብሏል፡፡ ሁኔታው በአካባቢው ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት ዘንድ መደናገጥን ፈጥሯል ተብሏል፡፡//

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe