በዋሻዎች ውስጥ የቀሩ የሃማስ ተዋጊዎች የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ወደ ቀጣዩ ማዕራፍ እንዳይገባ አድርገዋል ተባለ፡፡
200 የሚሆኑ የሃማስ ተዋጊዎች አሁንም በዋሻ ውስጥ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡ ይህም የጋዛው የተኩስ አቁም ስምምነት ወደፊት እንዳይራመድ እንቅፋት መፍጠሩ ተገልጻል፡፡
እነዚህ የሃማስ ተዋጊዎች በእስራኤል ቁጥጥር ስር በሚገኘው የራፋህ ከተማ ደቡባዊ ክፍል በሚገኙ ዋሻ ውስጥ እንዳሉ ይታመናል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
አሸማጋዮች እክል የገጠመው የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ወደሚቀጥለው እና የበለጠ ውስብስብ ምዕራፍ ለማራመድ በሚያደርጉት ጥረት አዲስ እንቅፋት እያጋጠማቸው ባለበት በዚህ ስዓት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ልዩ አምባሳደር ኩሽነር ሰኞ እለት እስራኤል መግባታቸው ይታወቃል፡፡
እስካሁን የሃማስ ትጥቅ መፍታት፡የጋዛ መልሶ ግንባታ እና የወደፊት አስተዳደር የሚሉ ጉዳዮች እልባት አላገኙም፡፡//

