በዩኔስኮ ጊዜያዊ መዝገብ ላይ የተመዘገበው የባሌ ተራራሮች ብሔራዊ ፖርክ አደጋ ላይ ነው

በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ብዝሃ ሕይወት ላይ እየደረሰ የሚገኘውን አደጋ ለመከላከል የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር እንደሚያስፈልግ የፓርኩ አስተዳደር ገለጸ።ልቅ ግጦሽ፣ የደን ጭፍጨፋና ሕገወጥ ሰፈራ የፓርኩን ህልውና ጭምር እየተፈታተኑ ከሚገኙ ችግሮች መካከል መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ሻሚል ከዲር  እንደገለጹት በፓርኩ ውስጥ በሚገኙ አያሌ የእንስሳትና የእጽዋት ብዝሃ ሕይወት ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ችግር ለመከላከል የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ይጠይቃል፡፡

Read also:ፈረንሣይ በ50 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ ለኢትዮጵያ   የሳተላይት ማምረቻና መገጣጠሚያ ማዕከል ልትገነባ…

በተለይ የፓርኩን ህልውና ጭምር እየተፈታታኑ የሚገኙት የልቅ ግጦሽ፣ የደን ምንጣሮና ሕገወጥ ሰፈራን ለመከላከል የመንግሥት አካላት ቁርጠኝነትን ይጠይቃል።

ተወካዩ እንዳሉት ፓርኩን ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ ባለፉት ዓመታት በአካባቢው የሚገኙ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ርብርብ ቢያደርጉም ከችግሩ ስፋትና ጥልቀት አንጻር ብዙ መሥራትን ይጠይቃል።

ፓርኩ ውስጥ በሚገቡ እብድ ውሾች በሚተላለፈው በሽታ ምክንያት ባለፉት ሁለት ዓመታት የቀይ ቀበሮ ቁጥር እየተመናመነ መምጣቱን የገለጹት ደግሞ በፓርኩ የቀይ ቀበሮ ፕሮግራም ከፍተኛ ባለሙያ አቶ እድሪስ ኤቡ ናቸው፡፡

Read also:ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ  ምክያት ከ139 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ባለይ የሚገመት…

የዲንሾ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ አብዱረኡፍ ኡስማን የአካባቢው ነዋሪዎች በፓርኩ ላይ የሚያደርሱትን ተጽእኖ ለመቀነስ አማራጭ የኑሮ መደጎሚያ ስልት ሊቀርብላቸው ይገባል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

መንግሥትና ሌሎች በፓርኩ ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ትኩረት እንዲሰጡትም ጠይቀዋል።

የባሌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ዲደ ጉደታ በዞኑ ፓርኩን በሚያዋስኑ ወረዳዎች ውስጥ የሚታየው ህገ ወጥ ሰፈራና የደን ጭፍጨፋ ለማስቆም ግንዛቤ ከመፍጠር አንስቶ ሕጋዊ እርምጃዎች በመውሰድ ጭምር ለማስተካከል ጥረት ሲደረግ ቆይቷል ይላሉ፡፡

ለዱር እንስሳትም ሆነ ለአካባቢው ሥነ-ምህዳር እየፈጠረ ያለውን ይሄን ትልቅ ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት እስከ ቀበሌ በተዋቀረው አደረጃጀት በመጠቀም ፓርኩን ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ የተጀመሩ ተግባራትን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

Read also:ኢጋድ የኮቪድ 19 ወረርሽንን ለመከላከል 25 ሺህ ዶላር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁሶችን…

ምክትል አስተዳዳሪው እንዳሉት ፓርኩ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ሰው ሰራሽ አደጋ ለመቅረፍ ከፓርኩ የሚፈልቁ ምንጮችን በመስኖ ለማልማት የሚያስችሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለአካባቢው ማኅበረሰብ አማራጭ የገቢ ምንጭ ለመፍጠር በፌዴራልና በክልሉ መንግሥት በትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝም አስረድተዋል ።

በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሣይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ጊዚያዊ መዝገብ ላይ የሰፈረው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የደጋ አጋዘንና ቀይ ቀበሮን ጨምሮ የበርካታ ዱር እንስሳት፣ አእዋፋትና ዕፅዋት መኖሪያ  ነው።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe