በደቡብ አፍሪካ በፖሊስ ታግተው የነበሩ 22 ኢትዮጽያዊያን ከእገታው ነጻ መሆናቸው ተሰማ፡፡ ፖሊስ የህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሰለባ ሳይሆኑ አልቀረም ያላቸውን ኢትዮጽያዊያን አግቷቸው ቆይቷል፡፡
የሀገሪቱ ፖሊስ እንዳለው እነዚሁ እድሚያቸው ከ16 እስከ 26 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ኢትዮጽያዊያን የህገ-ወጥ ሰዎች አዘዋዋሪዎች ሰለባ ሳይሆኑ እንዳልቀረ ይፋ አድርጓል፡፡
ፖሊስ ትላንት ባደረገው ፍተሸ 22ቱ ኢትዮጽያዊያን በአንድ ክፍል ውስጥ ተዘግቶባቸው ነበር ያገኘው፡፡ በወቅቱ 3 የሚሆኑት ኢትዮጽያዊያን የነበሩበት የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ስለ ነበር ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ ማድረጉንም ገልጻል፡፡
ጥቂቶቹ በዚህ ሁኔታ እስከ 8 ወር ድረስ የቆዩ መሆናቸውንም አመልቷል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት 44 ኢትዮጽያዊያን በተመሳሳይ ሁኔታ በአንድ ክፍል ውስጥ ተዘግቶባቸው በፖሊስ መገኘታቸውን ሰምተን ነበር፡፡

