በዶክተሩ ፍቅረኛዬ ጉድ ሆንኩ፤ የምትለው ወጣት 2 አመት አስፈረደችበት

በዶክተሩ ፍቅረኛዬ ጉድ ሆንኩ ሙያውን ተጠቅሞ ህይወቴን አመሰቃቀለው በማለት ከወራቶች በፊት ታሪኳን አጋርታ የነበረችው ወጣት በአዲስ ነገር መጥታለች፡፡ ለመሆኑ ምን ይዛ መጣች ትሰሙታላችሁ፡፡// ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከቻይና ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች በሱስ ምክኒያት ስለተባረረውና ሰሞኑን ማህበራዊ ሚዲያው ላይ መነጋገሪያ ስለሆነው ግለሰብም ትሰማላችሁ፡፡//

በተጨማሪ ከ460 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ ፈጅታለች የተባለች አውሮፕላን በአንድ ድርጅት ወደ ሀገር ውስጥ መግባቷንና በሽረ እንደስላሴ ከተማ 250 ሰዎች በሽሻ ቤት ውስጥ መያዛቸውን ፖሊስ ገልጻል፡፡// ሁሉንም ጉዳዮች በዝርዝር እናስደምጣችኋለን፡፡//

በዶክተሩ ፍቅረኛዬ ጉድ ሆንኩ፤ህይወቴ ተመሰቃቀለ በማለት ከወራት በፊት ታሪኳን አጋርታ በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ የነበረችው ወጣት በአዲስ መረጃ መጥለች፡፡

የወጣት ረዴት ለማ ጉዳይ ብዙዎችን ሲያነጋግር፤ብዙዎችንም በእንባ ሲያራጭ የቆየ ታሪክ መሆኑ ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ከፍቅረኛዋ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት የመደብደብ ጉዳት ደርሶባት የጎን አጥንቶቿ ተሰብረው እንደነበር መግለጻ ይታወሳል፡፡

ታዲያ ችግሩ የሚፈጠረው እዚህ ጋር ነው፡፡ ረዴት ዶክተሩ ጓደኛዋ ሲሰጣት የነበረው መድሃኒት ለህክምና ሄዳ የታዘዘላትን መድሃኒት አልነበረም፡፡ ይሄ መድሃኒት ነበር የረድኤትን የሂወት አቅጣጫ የለወጠው፡፡ መድሃኒቱ ለእርሷ የማይሰጥና ከአንድ ጊዜ በላይ ከተወሰደ ደግሞ ሱስ የሚሆን ነበር፡፡ ረድኤት ለ21 ቀናት ጓደኛዋ መድሃኒቱን እንደሰጣት ተናግራለች፡፡ እርሱ መስጠጡቱን ሲተወውም እራሷን በሯሳ መውጋት ጀመረች፡፡ ከዚህ በኋላ ፍጹም ወደማትወጣው ነገር ውስጥ ገባች፡፡ መድሃኒቱ ደስታን፡ፍርሃትን፡ለምንም ነገር ደንታቢስ መሆንን ነበር ያስከተለባት፡፡ እርሱን ሳትወስድም በጭራሽ እንዳትውልም አደረጋት፡፡ በየቀኑ ለመድሃኒቱ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ገንዘቦችን ወጭ እንድታደርግ ያስገድዳትም ነበር፡፡

በዚህ የተነሳ ራሷንም ለማጥፋት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን አድርጋለች፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን በሆዷ ጽንስ ይዛ ነበር፡፡ ደግሞ ገና 24 ዓመቷ ነበር፡፡

ረድዔት ዶክተሩ ፍቅኛውን ከመተዋወቋ በፊትም አሜሪካን ሀገር ይኖር የነበረ ፍቅረኛ እንደነበራትም ገልጻ ነበር፡፡ ከዶክተሩ ፍቅረኛዋ ጋርም በአንድ ወቅት ህክምና ለማግኘት ወደ ሆስፒታል በሄደችበት አጋጣሚ ነበር የተዋወቁት፡፡

የረዕዴት ታሪክ የብዙዎች ታሪክ ሆኖ ደግሞም መነጋገሪያነቱ ሳበርድ ለረጅም ወራት ዘልቆ ነበር፡፡

ጉዳዩም ወደ ህግ አምርቶ የቀድሞ ዶክተሩ ፍቅረኛዋ በሁለት ዓመት እስር እና በ10ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ መፈረዱን ነው ይፋ ያደረገችው፡፡

ፍርዱን ብቀበለውም የእርሱ ወገኖች ነን የሚሉ አካላት ግን ማስፈራሪያዎችን እያደረሱባት መሆኑን ገልጻለች፡፡

አሁን መድሃኒቱን ሙሉ በሙሉ መውሰድ ማቆሟን ገልጻ፤መድሃኒቱ ያስከተለባት ጉዳት ግን እንዳለ ተናግራለች፡፡ ረዴት የሰባት ወር ህጻን ልጅ እናት መሆን መቻሏንም ገልጻለች፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe