በጦርነቱ 8 ሺህ 500 ትምህርት ቤቶች መውደማቸው ተሰማ

” 2 ሚሊየን የሚደርሱ ህፃናት  ከትምህርት ገበታቸው ውጭ ሆነዋል ” – ሮላንድ ኮቢያ

የአውሮፓ ህብረት በጦርነት ምክንያት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል እና ለተማሪዎች ምገባ የሚውል የ33 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን ኤፍ ቢሲ ዘግቧል።

ጦርነቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች 8 ሺህ 500 ትምህርት ቤቶች መውደማቸውና 1 ሺህ 500 ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ 2 ሚሊየን የሚደርሱ ህፃናት  ከትምህርት ገበታቸው ውጭ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ለሰላም ስምምነቱ በሚደረገው ጉዞ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ድጋፉ  የትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ የምገባ ፕሮግራም፣  የንፅህና መጠበቂያ፣  የጤና እና መሰል አገልግሎት ለተማሪዎች ተደራሽ በማድረግ ጥራት ያለው ትምህርትን ለመተግበር የሚደረገውን ጉዞ ያግዛል ብለዋል።

ዓለም አቀፉ የህጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከህብረቱ ጋር በጋራ እንደሚያስፈፅሙት ተጠቁሟል።

በድጋፉ 80 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻል የተገለጸ ሲሆን 60 ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡ መጠቆሙን የኤፍ ቢ ሲ ዘገባ ያስረዳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe