ትራምፕ ከቻይናው አቻቸው ጋር ታሪካዊ የተባለ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ይህ ስምምነት በዓለም አቀፍ የነዳጅ እና የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኖ የነበረውን የሆርሙዝ የባህር መስመር በቋሚነት ክፍት ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የአሜሪካ መንግስት ለቻይና ለሌላው ዓለም ጥቅም ሲባል ስትራቴጂካዊ የባህር መስመር በቋሚነት ክፍት ሆኖ እንዲቆይ ወስኗል ተብሏል፡፡
ቻይና በበኩሏ ወደ ኢራን የምታደርገውን ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ልውውጥ ለማቆም ተስማማታለች ነው የተባለው፡፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከቻይናው አቻቸው ጋር ውጤታማ ግንኙነት እያደረጉ መሆኑን ገልጸው፤በቅርቡም ወደ ቤጂንግ እንደሚያቀኑ አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በማህበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤አሜሪካ በማንኛውም ወታደራዊ ፍልሚያ ላይ ያላትን የበላይነት አጽንኦት ቢሰጡም፤ግጭት ከመፍጠር ይልቅ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፍትሔ መፈለግ ለሁሉም ወገን የተሻለ መሆኑን አንስተዋል፡፡//
ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ አዲስ የሰላም እቅድ ለአሜሪካ ማቅረቧ ተሰማ፡፡
በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ያለው ውጥረት በከረበበት በዚህ ወቅት ቴህራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ለሚያልፉ መርከቦች ደህንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ ለመፍቀድ የሚያስችል እቅድ ማቅረቧን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ኢራን በኦማን የባህር ክልል በኩል የሚጓዙ መርከቦች ያለምንም ጥቃትና መስተጓጓል እንዲያልፍ ለመፍቀድ ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወሽመጡ ለማስከፈት ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ጫና እየደረሰባቸው ሲሆን ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተንና በቴህራን መካከል የተደረገው ድርድር ያለ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
ቴህራን ይህንን እቅድ ተግባራዊ የምታደርገው ለአሜሪካ ያቀረበቻቸው ጥያቄዎች ምላሽ ካገኙ ብቻ መሆኑ ተነግሯል፡፡//

