ቡና ባንክ “አቦል ደሞዜ ” የተሰኘ የቅድመ ደሞዝ ብድር አገልግሎት በይፋ አስጀመረ

ቡና ባንክ እና ካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ “አቦል ደሞዜ ” የተሰኘ የቅድመ ደሞዝ ብድር አገልግሎት በይፋ አስጀመሩ
ቡና ባንክ እና ካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ የቅድመ ደሞዝ ብድር አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ “አቦል ደሞዜ” የተሰኘ የዲጂታል ብድር እና ቁጠባ አገልግሎት በዛሬው እለት በይፋ አስጀምረዋል ።
ለተቀጣሪ ደመወዝተኛ የህብረተሰብ ክፍል አገልግሎት እንዲሰጥ የተነደፈው “አቦል ደሞዜ” ለሰራተኞች የደሞዝ መደረሻ የገንዘብ ፍላጎትን ለማርካት የተዘጋጀ የቅድመ ደመወዝ ብድር አገልግሎት ሲሆን ሰራተኞች ከክፍያ ቀናቸው በፊት በሚገጥማቸው የገንዘብ እጥረት ወቅት የወር ደሞዛቸውን የተወሰነ ክፍል ያለምንም ማስያዣ በብድር እንዲያገኙ የሚያስችል የፋይናንሺያል አገልግሎት እንደሆነ በማስጀመሪያ መርሀግብሩ ላይ ተገልጿል።
በዚህ አዲስ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የደመወዛቸውን 33% ወይም 50% በቀላሉ ካሉበት ሆነው በካቻ የሞባይል አፕሊኬሽን ማግኘት ሲችሉ ምቹ በሆነ የአከፋፈል ዘዴ በተቀመጠው ቀነ ገደብ መሰረት ብድራቸውን መክፈል የሚችሉበት አማራጭም ተቀምጦላቸዋል ተብሏል።
ሰራተኞች አገልግሎቱን ለማግኘት የቡና ባንክ ወይም የካቻ ደንበኞች መሆን እንደሚጠበቅባቸው የቡና ባንክ ቺፍ ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ መንክር ሀይሉ የገለፁ ሲሆን ”አቦል ደሞዜ” የደንበኞቻችንን ተለዋዋጭ ፍላጎት የሚያሟሉ አዳዲስ እና ተደራሽ የሆኑ የፋይናንስ መፍትሄዎችን ለማቅረብ ያለንን ቁርጠኝነት ያንፀባርቃል” ነው ያሉት ።
አገልግሎቱን ያበለፀገው የካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሀም ጥላሁን በበኩላቸው “ካቻ በተለመደው የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ያልነበረውን ሰፊ የህብረተሰብ ክፍል ለማገልገል የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን እንደ አማራጭ ይዞ የመጣ ኩባንያ መሆኑን ገልጸዋል
ከተመሰረተ 15 ዓመታት ያስቆጠረው ቡና ባንክ በባንክ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ላለፉት 15 ዓመታት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝና ከ4 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ያፈራ የፋይናንስ ተቋም ነው

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe