ቡና ባንክ ከግብር በፊት ወደ 1 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ትርፍ አተረፈ

ቡና ባንከ አ.ማ ዓመታዊውን የባለአክሲዮኖች 15ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አሁድ ታህሳስ 6 ቀን 2017 ዓ.ም አካሂዷል።
በአዲስ ፓርክ ሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደውና በርካታ ቁጥር ያላቸው ባለአክሲዮኖች በታደሙበት በዚሁ ጉባዔ ላይ የቡና ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ቢቀመንበር አምባሳደር ዓለማየሁ ሰዋገኝ የባንኩን የ2023/24 ዓመታዊ ሪፖርት ሰባለአክሲዮኖች በንባብ አቅርበዋል።
ሪፖርቱ በቀረበበት ወቅት እንደተገለጸው ባንኩ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ከግብር በፊት 930.1 ሚሊዮን ብር ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይ ይፋ አንደተደረገው ባንኩ አ.ኤ.አ ሰኔ 30 ቀ3 2024 በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ካለፈው በጀት ዓመት 20 በመቶ ዕድገት በማሳየት 43.87 በለዮን ብር ለደርስ ችሏል። ከዚህም በበጀት ከተሰበሰበው አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ውስጥ ከቁጠባ ሒሳብ 2.79 በቢሊየን በቢሊዮን ብር ፣ ከተንቀሳቃሽ ሂላብ 1.55 በሊዮን ብር ፣ ከጊዜ ገደብ ተቀማጭ 2.62 በሊዮን ብር የተገኘ ሲሆን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቶም 307.0 ሚሊዮን ብር ድርሻ እንዳላቸው ሪፖርቱ ያሳያል።
አምባሳደር ዓለማየሁ በንግግራቸው እንዳሰመሩበት ከሆነ ባለፈው የበጀት ዓመት እንደሃገር በተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ንረት ፣ በውጭ ምንዛሬ አጥረት፣ ተደራሪቢ የሆኑ የተቆጣጣሪ አካላት መመሪያዎች መውጣትና ተግባራዊ መሆን፣ እንዲሁም በተለያዩ ክልሎች የተከሰቱ ግጭቶችና ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት የፈጠረው የኑሮ ውድነት ሳቢያ የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ ተግዳሮት ተጋርጦበት ነበር ያሉ ሲሆን አነዚህ ችግሮች የባንኮችን የማበደር ብቻ ሳይሆን ተቀማጭ የማሰባሰብ አንቅስቃሴም በእጅጉ ፈትነውታል። ይህም በውጤቱ የባንኮችን የመክፈል እና የማበደር አቅም በእጀጉ ተፈታትኖታል።
አክለውም ይሁንና ባንካችን በኢንደስትሪው ላይ የተጋረጡትን ፈተናዎች ተቋቀሞ በዚህ ጠንካራ ውድድር ውስጥ መዝለቅ በመቻሱም አትራፊነቱን አስጠብቆ ቀጥሏል ብለዋል።
በቦርድ ለቀመንበሩ የቀረበው ሪፖርት ላይ እንደተመለከተው ባንኩ በዓመቱ ውስጥ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በአጠቃላይ 4.1 በሊዮን ብር አበድሯል። ይህም ቡና ባንክ በአጠቃላይ በተለያየ የኢኮኖሚ ዘርፎች ያበደረውን የገንዘብ መጠን በ11.8 በመቶ በማሳደግ 38.87 በሊዮን ብር አድርሶታል።
ከውጭ ሃገር የሚላክ ሀዋላ ከላይ በተገለጹት ዓለምአቀፋዊና ሃገራዊ ችግሮች ባስከተሉት ተጽእኖ ሳቢያ መቀነሱ እንዲሁም የኤክስፖርት ስራ ጉልህ በሆነ መልኩ መቀዛቀዙ በውጭ ምንዛሪ ግኝት በኩል የባንኩን አፈፃፀም በታቀደው መልኩ እንዳይከናወን አሉታዊ ጫና ያሳደረ ሲሆን የቦርድ ሊቀመንበሩ ሪፖርት እንደሚያሳየው በዓመቱ የባንኩ የውጭ ምንዛሬ ግኝት 167.6ሚለዮን የአሜሪካን ዶላር መሆኑንም ጠቁሟል።
በቦርዱ ሊቀመንበር አምባሳደር ዓለማየሁ ሰዋገኝ ሪፖርት ውስጥ ከተካተተው አንዱ የባንኩን ጠቅላላ ሃብት የተመለከተ መረጃ ሲሆን አንደሪፖርቱ የባንኩ ጠቅላላ ሃብት በበጀት ዓመቱ የ8.14 በሊዮን ብር ዕድገት አሳይቶ 54.53 ቢሊዮን ብር ደርሷል።
ሊቀመንበሩ ባቀረቡት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ላይ እንደተብራራው የባንኩ የተከፈለ ካፒታል በበጀት ዓመቱ የብር 549.2 ሚሊየን ብር እድገት አሳይቷል። ይህም የባንኩን አጠቃላይ የተከፈለ ካፒታል መጠን 4.83 ቢሊዮን ብር አድርሶታል፡፡
በቀረበው ሪፖርት ቡና ባንክ ለደንበኞቹ ያለውን ተደራሽነት ብሎም የተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰቡን ሥራ በማሳደግ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ በመቀጠል ምቹ የባንክ አገልግሎቶችን በማቅረብና አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት ረገድ በተደረገው አንቅስቃሴ ባንኩ በበጀት ዓመቱ የተቀማጭ ሂሳብ ደንበኞቹን ቁጥር በ 968 ሺ 819 ከፍ በማድረግ የ31.8 በመቶ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሱም ተብራርቷል። ይህም አፈጻጸም የባንኩን አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ወደ 4 ሚልየን 019 ሺ 072 ከፍ አድርጎታል።
ከተመሰረተ 15 ዓመታትን ያስቆጠረው ቡና ባንክ ከ14 ሺህ በላይ ባለአከሲዮኖችና ከ4100 በላይ ቋሚ ሰራተኞች ያሉት በመላው የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ 474 ቅርንጫሮቹ የኮንቬንሽናል፣ ዲጂታል እንዲሁም ከወለድ ነጻ የባንከ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ባንክ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe