ቢል ጌትስ ካለው 200 ቢሊዮን ዶላር ሃብት ውስጥ አብዛኛውን ለአፍሪካ ሊሰጥ መሆኑን በአዲስ አበባ ቆይታው ተናገረ

የማይክሮሶፍት ዌር መስራች ቢልጌትስ በቀጣዩቹ 20 ዓመታት ካለው ሃብት ውስጥ አብዛኛውን በአፍሪካ የጤና እና ትምህርት አገልግሎቶችን ለማሻሻል እንደሚያውል ተናግሯል፡፡

የ69 ዓመቱ ባለጸጋ ፡በጤና እና ትምህርት የሰው ልጅን በማውጣት አፍሪካ ውስጥ እያንዳንዱ ሀገር በብልጽግና ጎዳና ላይ መሆን አለበት ብሏል፡፡

ቢል ጌትስ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት በተካሄደ ስነ ስርዓት የሀገሪቱን ታላቅ የክብር ኒሻን ሽልማት መቀበላቸው ይታወሳል፡፡

ቤልጌትስ ከ20 ዓመት በላይ በኋላ 200 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ከሚጠበቀው ሀብቱ ውስጥ 99 በመቶውን ለመስጠት ማቀዱን ያስታወቀው ባለፈው ወር ነበር፡፡

በአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት በተዘጋጀው ስነ ስርዓት ላይ በቀጣዩቹ 20 ዓመታት ውስጥ ያለኝን ሀብት እንደሚከፋፈል ቃል ገብቻለሁ፡፡ አብዛኛው ገንዘብ አፍሪካ ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችን እንድትፈቱ ለማገዝ ይውላል በማለት ተናግሯል፡፡ ቢል ጌት 99 በመቶ የሚሆነውን ሃብቱንም አካፍሎ በዓለም አምስተኛው ሃብታም ሰው ሆኖ እንደሚቀጥል ተነግሯል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe