ቡና ባንክ በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አካሄደ

  • ቡና ባንክ በአካባቢ ጥበቃና በአረንጓዴ ልማት ስራዎች ላይ መሳተፉን አስታወቀ፡፡

ቡና ባንክ ከአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር፣ በኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ማዕቀፍ ውስጥ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላና የአካባቢ ጥበቃ ተግባራትን በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በጎነት መንደር አካሄደ።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና የአረንጓዴ ልማትን ለማስፋፋት በየዓመቱ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሮችን ታከናውናለች። በዚህ አገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ማዕቀፍ ውስጥ፣ ቡና ባንክ በበኩሉ ለምግብነት የሚውሉ የአቮካዶና ዘይቱና ችግኞችን በመትከል የከተማዋን ውበት ለማሳደግ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋምና ዘላቂ ልማትን ለማስፈን የሚደረገውን አገር አቀፍ ጥረት የሚያግዝ ተግባር አከናውኗል።

ይህ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር የተፈጥሮ- አካባቢን ውበት በመጠበቅ፣ ለነዋሪዎች ጤና ተስማሚ የሆነ አካባቢ ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያግዝ ነው ሲል ባንኩ ገልጿል።  ባንኩ በዚህ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር መሳተፉ፣ በፋይናንስ ዘርፍ ካለው ቀዳሚ ሚና ባሻገር፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ለማህበረሰብ ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ ተግባር ነው።

ስለሆነም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር የኢትዮጵያን ዘላቂ ልማት ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ቡና ባንክ ይህን ተግባር በመደገፍ ለአካባቢ ጥበቃና ለማህበረሰብ ልማት ያለውን ኃላፊነት እየተወጣ ይገኛል። ባንኩ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ራዕይ እውን ለማድረግ በሚደረገው አገር-አቀፍ ጥረት ውስጥ በተመሳሳይ መርሀ-ግብሮች ተሳትፎውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።

ይህ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ለማህበረሰባችን ኑሮ ተስማሚ አካባቢን ለመፍጠርና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የምናደርገው የጋራ ጥረት መገለጫ ነው ያለው ባንኩ በቀጣይም የልደታ ክፍለ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤትን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሌሎች የችግኝ ተከላና የአካባቢ ጥበቃ መርሀ-ግብሮች ላይ ለመሳተፍ ዝግጁነቱን ገልጿል።

ቡና ባንክ ከ14ሺህ በላይ የሚሆኑ ባለአክሲዮኖች ያሉት፣ ከ15 ዓመታት በፊት የተቋቋመና በኢትዮጵያ ሁሉም ክልሎች በ454 ቅርንጫፎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የባለራዕዮች ባንክ ነው፡፡ ባንካችን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አቅምን ያገናዘበ ልዩ ልዩ የቁጠባና ብድር አገልግሎቶችን በማቅረብ ተዓማኒነትን ያተረፈ ባንክ  ስለመሆኑ ከቡና ባንክ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንና ፕሮሞሽን ዋና ክፍል የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe