ተወዳጇ ድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ የመጨረሻዬ ነው ያለችውንና 7 ዓመት የፈጀውን አልበም በዚህ ሳምንት ለአድማጭ ልታደርስ ነው፡፡
ኩኩ ሰብስቤ ደጃዝማች የተሰኘው አልበም ሲሰራ ያለቀሰችበት አጋጣሚዎች እንደነበሩም ገልጻለች፡፡ ሰባት ዓመት ፈጅቷል የተባለው ደጃዝማች አልበም ቴዲ አፍሮ 8 ሙዚቃዎችን በዜማና ግጥም እንዲሁም በአጃቢነት እንደተሳተፈም ታውቋል፡፡
ድምጻዊት ኩኩ ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ስራ ለሌላ ሙዚቀኛ ሲሰጥ እስከ መጨረሻው ድረስ እንደራሱ አድርጎ፤ሌሊት ሳይቀር እያደረ የሚሰራ ነው፤ይህንንም በዚህ አልበም ላይ አሳይቷል ነው ያለችው፡፡ አልበሙ በጥሩ ስሜት የሰራ መሆኑን ተናግራለች፡፡ ከዚህ ውጭ ግን በተደጋጋሚ ቀጠሮ ምክኒያት ከአቀናባሪው አቤል ጻውሎስ ጋር ልትጣላበት የነበረበት እና የሙዚቃውን ስራንም ከእርሱ ጋር ለመስራት የገባችውን ውል ልታቋርጥ ሁላ እንደነበረ ኋላ ግን በህመም ምክኒያት እንደሆነ ስትረዳ ሁሉንም ነገር እንደተወችውና እርሱንም ስታስታምም እራሷን እንዳገኘችው አንጋፋዋ ሙዚቀኛ ኩኩ ሰብስቤ ስለ ስራው አጋጣሚ ስታወራ ገልጻለች፡፡
8ተኛዋ የሆነው ደጃዝማች አልበም የተለየ እንደሆነም ገልጻለች፡፡አንጋፋው የግጥም ደራሲ ይልማ ገብረዓብ፡ቴዲ አፍሮ፡ናትናኤል ግርማቸው፡መሠለ ጌታሁን፡መሠለ አስማማው እና ፍሬዜር አበበወርቅ በግጥምና ዜማ ተሳትፈውበታል፡፡
ከዚህ በኋላ በነጠላ ዜማ ካልሆነ በአልበም ደረጃ እንደማትመጣ አስታውቃለች፡፡ ኩኩ ሰብስቤ በቀደመው ጊዜ አልበም ሰርቶ ለማጠናቀቅ አስራምስት የስራ ቀናት ብቻ እንደሚበቃ አስታውሳ፤ የአሁኑ ደጃዝማች አልበም ግን 7 ዓመት እንደፈጀባት ተናግራለች፡፡
ታዋቂው ሙዚቃ አቀናባሪ አቤል ጻውሎስ የአልበሙን አብዛኞቹን ሙዚቃዎች እንዳቀናበረ እና አሬንጅመንቱንም እንደሰራው ተነግሯል፡:
ለዓለም አቀፍ አድናቂዎቿ በላከችው ሞቅ ያለ እና ልባዊ መልእክት ኩኩ እንዲህ ብላለች:
“ሰላም ለምወዳችሁ አድናቂዎቼ እና ወዳጆቼ በሙሉ በዓለም ዙሪያ! ከረጅም እረፍት በኋላ፣ አዲሱ አልበሜ “ደጃዝማች” ሚያዝያ 24 ቀን 2017 እንደሚለቀቅ ስገልጽላችሁ በታላቅ ደስታ ነው።”
“ደጃዝማች” የሚለው ርዕስ በታሪክ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታደራዊ እና የመኳንንት ማዕረግ ሲሆን ጥንካሬን፣ አመራርን እና የባህል ቅርስን የሚያመለክት ሲሆን እነዚህም በአልበሙ ውስጥ በዋናነት የተንጸባረቁ ጭብጦች ናቸው። የኩኩ መመለስ በኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ በጥልቅ ስር የሰደደ የግል እና የጥበብ መግለጫ ሲሆን ዘመናዊ የሙዚቃ ድባብን ያካትታል።
አድማጮች የኩኩን ልዩ የድምፅ አገላለጽ እና የግጥም ጥልቀት ባካተተ መልኩ በባህላዊ የኢትዮጵያ ዜማዎች እና በዘመናዊ የሙዚቃ ተጽዕኖዎች የበለፀገ ውህደት ሊጠብቁ ይችላሉ። “ደጃዝማች” ለረጅም ጊዜ የቆዩ አድናቂዎችን እና አዲስ ትውልድን ለማስተጋባት እና በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የባህል ምዕራፍ ለመሆን ተዘጋጅቷል።
አልበሙ ቀድሞውንም ከፍተኛ ግምት እየተሰጠው ሲሆን፣ መለቀቁም በሙዚቃ አፍቃሪዎች፣ በባህል ወዳዶች እና በመገናኛ ብዙኃን ዘንድ በቅርብ እየተከታተለ ነው። በአመቱ ከሚለቀቁት በጣም አስፈላጊ የኢትዮጵያ አልበሞች መካከል አንዱ እንደሚሆን በሰፊው ይጠበቃል።

