የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር ከጥቁር ባህር አቅጣጫ የተነሳ እና የቱርክንም የአየር ክልል ለመጣስ ሞክሯል ያሉትን ድሮን መትቶ መጣሉን አሳውቋል። ቱርክ ሰው አልባ አውሮፕላኑ የማን እንደሆነ የገለጸችው ነገር ባይኖርም፤የአየር ክልሏን ለመከላከል ሲባል እንደመታችው ነው ይፋ ያደረገችው።
ይህ ክስተት የተሰማው ባለፈው ሳምንት ቱርክ በጥቁር ባህር አካበቢ እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት በተመለከተ ማስጠንቀቂያ ከሰጠች በኋላ ነው።
ሩሲያ በዚሁ ባህር የዩክሬን ወደብ ላይ ጥቃት አድርሳ ሦስት ባለቤትነታቸው የቱርክ የሆኑ እቃ ጫኝ መርከቦች የጥቃት ኢላማ ከተደረጉ በኋላ የተፈጠረ ነው።
የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር ሰው አልባ አውሮፕላኗን መጣሉን ለመግለጽ ባወጣ መግለጫ ላይ የሀገሪቱ እና የኔቶ ኤፍ 16 ተዋጊ ጄቶች የቱርክን የአየር ክልልን ደህንነት ለመከታተል እነሰሩ መሆናቸውን ጨምሮ ገልጿል።
ተመቶ የተጣለው ሰው አልባ አውሮፕላን ከቁጥጥር ውጪ የነበረ ስለመሆኑ ሮይተርስ አስነብቧል።
የቦላክሲ ቀጠና ቱርክ:ሩሲያንና ዩክሬንን ጨምሮ ስድስት ሀገራትን በድንበር የሚያዋስን ሲሆን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የእነዚህ ሀገራት የአየር ክልል የደህንነት ስጋት እየጨመረ መጥቷል። ቱርክ እና ረሲያ ጉርብትናቸው በምድር ላይ ድንበር ሳይሆን በጥቁር ባህር ነው።
የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር ድሮኑ ከየት ሀገር የተነሳች እንደሆነ:መጥኑ እንዲሁም ወታደራዊ ይሁን አልያም ሲቪሊያን በዝርዝር ያለው ነገር የለም።//

