ቶንሲል ምንድን ነው?

ቶንሲል ለብዙዎቻችን እንደሚመስለን በሽታ አይደለም።
ቶንሲል ማለት ትንንሽ እንደ ኳስ ያሉ በጉሮሮ፣ ከአፍንጫ ጀርባ እና ከጉሮሮ በታች የሚገኝ የተፈጥሮ የበሽታ መከላከያ አካላት ስብስብ ነው።
➤ ቶንሲል ጥቅሙ ምንድን ነው?
በአፍም በአፍንጫም የሚገቡ ተዋህስያንን መዋጋት ነው። ስለዚህ የሰውነትን በር ከጠላት መከላከያ ነው።
➤ቶንሲል እና እንጥል አንድ ናቸው?
– ሁለቱም በላንቃ አካባቢ ይገኛሉ።
Uvula/እንጥል
እንጥል ማለት ከላንቃ ላይ የተንጠለጠለ ትንሽ ጡንቻ ማለት ነው።
➤ ሆኖም አንዳንዴ ከቶንሲል ህመም ጋር እንጥል ትንሽ መቅላት እና የማበጥ ነገር ሊኖር ይችላል ምክንያቱም ተመሳሳይ ባክቴርያ ወይም ቫይረስ ቦታውን በመያዝ ሊያስቆጣ ይችላል
➤ ስለዚህ እንጥልን ማስቧጠጥም ሆነ ማስቆረጥ በፍፁም አይመከርም !!
የህመም ምልክቶቹም
የሰውነት ትኩሳት
ለመዋጥ መቸገር
ራስ ምታት
የአንገት ንፍፊት እብጠት
ማንኮራፋት
የቶንሲል ህመም በትንፋሽ ጠብታ እና በንክኪ ይተላለፋል።
የባክቴሪያ ቶንሲል ከሁለት አመት በላይ የሆኑ ህጻናትን የሚያጠቃ ሲሆን አብዛኛዎቹ ከ5-15 እድሜ ያሉት ይጠቃሉ። የቫይረስ ሲሆን ለጋ ህጻናትም ይጠቃሉ።
ዶክተር ሸምሴ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe