ቻይና በየብስም፤በባህርም ማረፍ እና መነሳት ይችላል ላለችው አውሮፕላን የገበያ ፈቃድ ሰጥታለች፡፡
AG600 የሚል መጠሪያ የተሰተው አምፊቢየስ አውሮፕላን በቻይና ሲቪል አቪየሺን አስተዳደር የገበያ ፈቃድ ማግነቱ ነው የተነገረው፡፡
የውሃ ድራጎን የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ አውሮፕላን ግዝፈቱ እና ክብደቱ ትልቁ አምፊቢየስ አውሮፕላን እንዲሆን አስችሎታል ተብሏል፡፡
ይሔው አውሮፕላን በውሃ ላይ እና በደረቅ መሬት በተመሳሳ ጊዜ ማረፍ እና መነሳት እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡
አንድ ጊዜ በሞላው ነዳጅ 4ሺ500 ኪሎ ሜትር ርቀት መጓዝ ይችላል የተባለ ሲሆን፤ከባድ የሚባሉ የእሳት አደጋዎችን ለማጥፋት፡የባህር ላይ ፍለጋዎችን እና የነብስ አድን ስራዎችን ለማከናወን ይውላል ተብሏል፡፡

