ባለፈው ታህሳስ በሰርጉ ላይ በነበረ ጭፈራ ገንዘብ በመበተኑ የስድስት ወራት እስር ተበይኖበታል፡፡ ግለሰቡ ይህ ቅጣት የተላለፈበት የአገሪቱ መገበያያ ገንዝ የሆነውን ናይራን አቃልሏል በሚል ነው፡፡ ሜክአፕ አርቲስቱ ጥፋተኝነቱን ማመኑን ተከትሎ በካኖ ግዛት የሚገኝ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእስሩን ቅጣት በይኖበታል፡፡
ገንዘብ መበተን በናይጄሪያ በአብዛኛውን ጊዜ በሰርጎች እንዲሁም በሌሎች ክብረበዓላት ላይ ይከናወናል የተባለ ሲሆን፤ይህም ሰዎች ያላቸውን ሃብት ለማሳየት እንዲሁም ደስታቸውን ለመግለጽ የሚጠቀሙበት ነው፡፡
ነገር ግን የአገሪቱ የኢኮኖሚ እና ፋይናስ ወንጀሎች ኮሚሽን በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ጠቃሚ ምልክቶች አንዱ የሆነው ናይራን ክብሩን የሚያዋርድ ነው የሚል ዘመቻን ከፍቷል፡፡ አርቲስቱ 100ሺ ናይራ በሰርጉ ላይ በመበተኑ ነው ለእስር የተዳረገው፡፡/

