ብሉምበርግ የ2024 የአማችንን አምስት መቶ ቢሊየነሮች ዝርዝር ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ ዝርዝር በግንባር ቀደምነት የተቀመጠው ኤለን መስክ ሲሆን የሀብት መጠኑን አራት መቶ ሀምሳ ሁለት ቢሊዮን ዶላር መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃን የያዘው ጄፍ ቤዞስ ቢሆንም ከኤለን መስክ ጋር ያለው የሀብት ልዩነት ግን የሁለት መቶ ቢሊዮን ዶላር ልዩነት ያለው ሆኗል፡፡ የአማዞን መስራች የሆነው ቤዞስ ሀብት ሁለት መቶ አርባ ሶስት ቢሊዮን ዶላር መሆኑን የጠቀሰው ዘገባው በሶስተኝነት ማርክ ዙከርበርግ እንደሚከተለው አስረድቷል፡፡
በዚህ ዝርዝር ከአፍሪካ በሀብታቸው ቀዳሚ የሆኑት ደቡብ አፍሪካዊው ጆሀን ሩፓርት ሲሆኑ ናይጄሪያዊው አሊኮ ዳንጎቴ ይከተሏቸዋል፡፡ በአምስት መቶ የአለማችን ሀብታሞች በዚህ ዝርዝር ውስጥ ሼህ መሀመድ አልአሙዲም ተካተዋል፡፡
አልአሙዲ በዝርዝሩ ውስጥ የተቀመጡት በሶስት መቶ ሀያ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ነው፡፡ የሀብታቸው መጠንም ስምንት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር መሆኑን የጠቀሰው ብሉምበርግ ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር ሀብታቸው በሁለት መቶ ዘጠና ሚሊዮን ዶላር መቀነሱን ማስረዳቱን ዘ-ሐበሻ ከሪፖርቱ አይቷል።

