የአሜሪካ ብሔራዊ እዳ በአሥር ዓመት ውስጥ በእጥፍ ጨምሮ ከ40 ትሪሊዮን ዶላር በላይ መድረሱን የአገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አሳየ።
ይህም በዶናልድ ትራምፕ እንዲሁም በጆ ባይደን አስተዳደር ወቅትም አገሪቱ ለዓመታት ከፍተኛ ገንዘብ እንዳወጣች እና የወለድ ክፍያ መጠን እንደጨመረ ያሳያል።
በአውሮፓውያኑ 2016 ብሔራዊ እዳ ከ20 ትሪሊዮን ዶላር በታች ነበር።
ለምክር ቤት የበጀት እና ምጣኔ ሃብት መረጃ የሚያቀርበው የፌደራል ተቋም የሆነው ኮንግረሽናል በጀት ቢሮ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ በአውሮፓውያኑ 2026 መጨረሻ የአገሪቱ አጠቃላይ ብድር 39.6 ትሪሊዮን ዶላር ይደርሳል።
የአገሪቱ ብሔራዊ እዳ ከተጠበቀው በላይ በከፍተኛ መጠን መጨመሩ የመንግሥት ብድር እያደገ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑን እንደሚያሳይ ተገልጿል።
የአሜሪካ ብሔራዊ እዳ አሁን 41.1 ትሪሊዮን ዶላር እንደደረሰ እና በ2036 ወደ 64 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚጠጋ ኮንግረሽናል በጀት ቢሮ አስታውቋል።
የፌደራል መንግሥቱ የበጀት ጉድለትን ለመሸፈን በርካታ ገንዘብ ሲያወጣ፤ ሸማቾች በዋጋ ንረት እና በከፍተኛ ወለድ እየተፈተኑ ነው።
ይፋ የተደረገው ብሔራዊ እዳ፣ አጠቃላይ የቦንድ እዳን እንዲሁም በሁለቱ ፕሬዝዳንቶች የሥልጣን ዘመን የነበሩ ብድሮችን የሚያጠቃልል እንደሆነ ተገልጿል።
አሜሪካ ብሔራዊ እዳዋ ከ40 ትሪሊዮን ዶላር አለፈ
Sourcedere tube

