አሜሪካ አሁን ያላት የቀዶ ህክምና ሐኪሞች ላይ ለመድረስ ኢትዮጽያ 302 ዓመታት ይፈጅባታል ተባለ

በኢትዮጽያ የሚገኙ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች ቁጥር በመጭዎቹ ዓመታት አሁን ካለው በላይ እየቀነሱ ይሄዳል ተባለ፡፡

ኢትዮጽያ አሜሪካ አሁን ያላት የቀዶ ህክምና ሐኪሞች ላይ ለመድረስም 302 ዓመታትን ይፈጅባታል ነው የተባለው፡፡

በሚቀጥሉት ዓመታት በኢትዮጽያ የቀዶ ህክምና ሐኪሞች ቁጥር ከመጨመር ይልቅ አሁን ካለበት ይቀንሳል ሲል የኢትዮጽያ ቀዶ ህክምና ማህበር ገልጻል፡፡

ማህበሩ ይህን ያለው የ30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ባከበረበት ወቅት ነው፡፡ ኢትዮጽያ የቀዶ ህክምና ሐኪሞች ቁጥር በብዛት የያዘችበት ጊዜ አሁን ነው የተባለ ሲሆን አብዛኞቹም በከተሞች ውስጥ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በዚህ ስዓት የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ትምህርት ዘርፍ ከምርጫነት እየወጣ እንደሆነም ማህበሩ ጠቅሷል፡፡ ወደ ትምህርት ክፍሉም ዝቅተኛ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች ጭምር እንዲገቡ እየተደረገ እንደሆነ ገልጻል፡፡

በዚህ ወቅት በጠቅላላ ቀዶ ህክምና አንድም ተማሪ የሌላቸው ዩኒቨርሲቲዎች አሉ ተብሏል፡፡

ምንም እንኳን ቁጥሩ የተረጋገጠ ባይሆንም ያሉት የቀዶ ህክምና ሃኪሞች ቁጥር 1ሺ አካባቢ ናቸው ተብሏል፡፡ በሚቀጥሉት ዓመታት ቁጥሩ እየቀነሰ ሊሄድ እንደሚችል ማህበሩ ይፋ አድርጓል፡፡

ማህበሩ ይህን ያለው ባለፉት 3 እና 4 ዓመታት በዘርፉ ከተመረቁ የቀዶ ህክምና  ሐኪሞች ላይ አደረኩት ባለው ግምገማ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

ከአምስት እስከ አስር ዓመታት ባለው ጊዜ ራሳችሁን ምን ሁኔታ ላይ ታገኙታላችሁ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሥራየን ልተወው እችላለሁ፡ከሀገር እወጣለሁ የሚሉ መልሶችን ማግኘቱን ይፋ አድርጓል፡፡

ኢትዮጽያ አሁን ካላት የህዝብ ብዛት አንጻር የሚያስፈልጋት የቀዶ ህክምና ሐኪሞች ወደ 8ሺ ነው፡፡ አሁን ግን ያሉት ከ1ሺ አይበልጡም ነው የተባለው፡፡

ነገሮች አሁን ባሉበት ሁኔታ የሚቀጥሉ ከሆነም የዓለም ጤና ድርጅት ያስቀመጠው ልኬት ላይ ለመድረስ 302 ዓመታትን ይፈጃል ነው የተባለው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe