አሜሪካ ኢትዮጽያዊያንን ወደ ፓናማ አባረረች

አሜሪካ ኢትዮጽያዊያንን አባረረች፡፡ ተባረዋል የተባሉት ኢትዮጽያዊያንም በፓናማ ይገኛሉ ተብሏል፡፡ እነዚሁ ዜጎች አጣብቂኝ ውስጥ ስለመግባታቸውም ተሰምቷል፡፡

ኢትዮጽያዊያኑን ጨምሮ ሌሎች ከአፍሪካ እና ከእስያ ሀገራት የሄዱ ስደተኞች አሁን በላቲን አሜሪካዋ ሀገር ፓናማ በሆቴል ውስጥ እንዳይወጡ ተዘግቶባቸው ይገኛል ተብሏል፡፡

እነዚሁ ስደተኛ ዜጎች ከአሜሪካ ወደ ፓናማ ከተባረሩ በኋላ ስለቀጣይ እጣፈንታቸው እስካሁን ምንም የሚያውቁት ነገር አለመኖሩ ታውቋል፡፡

የፓናማ መንግስት በበኩሉ ቀደም ሲል ከአሜሪካ ሰነድ አልባ ተብለው ወደ ሀገሪቱ ከተባረሩት 299 ስደተኞች ውስጥ ከ190 በላይ የሚሆኑት በፈቃዳቸው ወደ ትውልድ ሀገራቸው መመለሳቸውን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጽያዊያኑም ወይ ወደ ሀገራቸው መመለስ አልያም የሚቀበላቸው ሦስተኛ ሀገር ከተገኛ ወደዚያ የመሻገር እድል ነው ያላቸው ተብሏል፡፡ እስካሁንም የሚቀበላቸው ሀገር እንዳላገኙ ታውቋል፡፡  ይህን ተከትሎም አጣብቂኝ ውስጥ መውደቃቸው ነው የተሰማው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe