አሜሪካ ዝነኛዋን ቲክቶከር ከሀገሯ አባረረች

ከ162 ሚሊዮን ህዝብ በላይ በቲክቶክ ተከታይ ያለው ትውልደ ሴኔጋላዊው ካቢ ሌም አሜሪካ እንደገባ ለእስር ተዳርጓል ነው የተባለው። ከስዓታት እስር በኋላም አሜሪካን ለቆ እንዲወጣ ተደርጓል። ካቢ ሌም በላስቬጋስ ኤርፖርት የኢሚግሬሽን ህጎችን ጥሷል በሚል በፖሊስ ቁጥጥር እንዲውል ከተደረገ በኋላ ዲፖርት ተደርጓል። የጣሊያን ዜግነትም ያለው የዓለማችን የቲክቶኮ ኮከብ የሚባለው ካቢ ላሜ አንድም ቃል ሳያወጣ በእጆቹ ብቻ ምልክት እያሳየ በሚሰራቸው ቪዲዮች ነው ዝናን ያተረፈው።

የ25 ዓመቱ ካቢ ላሜ የተወደው በሴኔጋል ሲሆን አሁን የጣሊያን ዜግነትን አግኝቶ በጣሊያን ይኖራል። ከቲክቶክ በተጨማሪ ከኢንስታግራም ከ80ሚሊዮን በላይ ተከታዮች አሉት። የሶሻል ሚዲያ ተዕፅኖ ፈጣሪው ካቢ የዩናሴፍ በጎ ፈቃደኛ አምባሳደርም ነው። ይህ ሁሉ እውቅናው ግን በአሜሪካ ከመታሰርና ዲፖርት ከመደረጉ አላተረፈውም።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe