አሜሪካ የኢራን 400 ኪሎ ግራም የበለጸገ ዩራኒየም ተላልፎ እንዲሰት ጠየቀች

ኢራን ከስምምነት እንድትደረስ የተሰጣት ጊዜ ሳትጠቀምበት እየሮጠባት ነው ሲሉ ትራምፕ ገለጹ።
በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ያለው ውጥረት አሁን ዳግመኛ ወደ ማገርሸቱ ተመልሷል፤የዲፕሎማሲ ዕድሎችም ወደ መጥበብ መጥተዋል።
ይህ ውጥረት የነገሰው ፕሬዝዳንት ትራምፕ አዲስ የሰጡትን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ እንደሆነም ታውቋል። አሜሪካ ከኢራን ጋር የኒውክሌር ድርድሩን ለመጀመር 400 ኪሎግራም የበለጸገ ዩራኒየም ተላልፎ እንዲሰጣት እንደ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጧ ተነግሯል።
ኢራንም በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ ያላት ሉዓላዊነት እንዲከበርላትና ጦርነቱ ላደረሰባት ኪሳራ ካሳ እንዲከፈላት እንደ ቅድመ ሁኔታ ጠይቃለችም ተብሏል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ መዓት ከመምጣቱ በፊት ጊዜን ተጠቅሞ ወደ ስምምነት መምጣት ይበጃል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
ትራምፕ ለቴህራን ባለስልጣናት ባስተላለፉት ማስጠንቀቂያ የመጨረሻው ስዓት እየቆጠረ ነው ብለዋል። ትራምፕ ይህንን ማስጠንቀቂያ ለቴህራን የሰጡት ኢራን ዋሽንግተን ዳግም ድርድር እንዲመጀመር የምትፈልገው እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ሲሟሉ ብቻ ነው በሚል በሚዲያ ይፋ ካደረገች ስዓታት በኋላ ነው።
ከቅድመ ሁኔታዎቹ መካከልም 400 ኪሎ ግራም የበለጸገ ዩራኒየም ተላልፎ እንዲሰጣቸው፤የጦር ካሳ እንዳይከፈልና የተያዙ ሀብቶቻችንም ባሉበት እንዲቀጥሉ የሚል ነው ፍላጎታቸው ስትል ቴህራን አስታውቃለች።
የፕሬዚዳንቱ ይህ አስተያየት የመጣው ቴህራን የዋሽንግተንን የሰላም እቅዶች እንድትቀበል ተደጋጋሚ ውትወታዎች በሚሰሙበት በዚህ ስዓት ነው።
ከእቅዶቹ መካከልም ኢራን ዩራኒየም ላለማበልጸግ እንድትስማማ: የበለጸጉ ዩራኒየሞችም ለአሜሪካ ጦር ማስረከብ እና የሆርሙዝ ሰርጥን ዳግም ክፍት ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል።
ዋሽንግተን በቀጠናው ያለው ግጭት የሚያበቃው በቅድሚ ድርድሮች ሲጠናቀቁ ነው ትላለች።
ቴህራን በቡኩሏ በቀጠናው በተለይም በሊባኖስ ያለው ወታደራዊ ዘመቻ እንዲቆም ማዕቀቦች ሲነሱና የተያዙ ሀብቶቼም ሲለቀቁ ብቻ ነው ጦርነቱ የሚያበቃው ትላለች።
በአደራዳሪዋ ፓከስታን አማካኝነት የተኩስ አቁም የተደረሰ ቢሆንም ይህ ስምምነት ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ማድረግ ሳይችል አሁንም ዘልቋል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe