አሜሪካ ጣልቃ የምትገባ ከሆነ ከፍተኛ አደጋ ሊከሰት ይችላል- አያቶላህ አሊ ሀሚኒ

በኢራን እና እስራኤል ግጭት አሜሪካ ወታደራዊ ተሳትፎ ካደረገች ከፍተኛ አደጋ ሊከሰት ይችላል ሲሉ የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሀሚኒ አስጠነቀቁ፡፡
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በፍጥነት እጅ እንድትስጥ ማሳሰባቸውን ተከትሎ የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሀሚኒ ሀገራቸው በቀላሉ የምትንበረከክ እንዳልሆነች ማስታወቃቸውን የሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
ስድስተኛ ቀኑን በያዘው የኢራን እስራኤል ግጭት ኢራን 400 የሚደርሱ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል በመተኮስ በቴል አቪቭ እና ሀይፋ ከተሞች የሚገኙ ህንጻዎች እና መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረሷ ይታወቃል፡፡
እስራኤል በበኩሏ በቀጠለችው የአየር ጥቃት የኢራን የኒውክለር ጣቢያዎችን ጨምሮ የሀገሪቱ ወሳኝ ተቋማት ማውደሟን ቀጥላለች፡፡
የሁለቱ ሀገራት ግጭት እየተባባሰ በመሄዱ በቴህራን እና ቴል አቪቭ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe