ቴህራን፡ሞስኮን እና ቤጂንግን ጨምሮ 10 አገራትን በሙሉ አባልነት ያቀፈው የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ በቻይናዋ ቲያንጂን ከተማ ሲደረግ ቆይቶ ትላንት ተጠናቋል፡፡ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ አገራቸው ከቻይና ጋር የድንበር ውዝግብ ውስጥ ከገባች በኋላ ሞዲ ከ7 ዓመታት በኋላ ነው ወደ ቻይና የገቡት፡፡ አራት የኒውክሌር ጦር የታጠቁ አገራት በአባልነት ያሉበት የትብብር ድርጅት ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡ ፕሬዝዳንት ሺጂንፒንግ በዚሁ ጉባኤ 20 የዓለም አገራት መሪዎችን አስተናግደዋል፡፡
የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ ፕሬዝዳንት ፑቲን እና የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናረንድራን ሞዲ በተገኙበት ሲከናወን ቆይቶቶ ተጠናቋል፡፡ ፕሬዝዳንት ሺ ለዚሁ ጉባኤ ከ20 በላይ የምዕራብ አገራት ያልሆኑ መሪዎችን ተቀብለው አስተናግደዋል፡፡
ፑቲን፡ሺ እና ሞዲ ትከሻ ለትከሻ ገጥመው ሲሳሳቁ ታይተዋል፡፡ የሻንጋይ የትብብር ድርጅት በዚህ ስዓት 10 ቋሚ አባል አገራትና ሁለት ታዛቢ አገራት ያሉት ነው፡፡
የሀገራቱ ስብስብም ከአጠቃላይ የዓለም ህዝብ ውስጥ ከ40 በመቶ በላይ ድርሻ እንዳለው ተነግሯል፡፡ ከ10 አባል አገራት መካከል አራቱ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ያላቸው አገራት ናቸው፡፡ እነርሱም ሩሲያ፡ቻይና፡ህንድና ፓኪስታን ናቸው፡፡
ቻይና እና ህንድ ድፍድፍ ነዳጅ ከሩሲ በመግዛት ቀዳሚዎቹ አገራት ናቸው፡፡ ሩሲያ ደግሞ ከዓለም ሁለተኛዋ ድፍድፍ ነዳጅ በመሸጥ የምትጠቀስ አገር ነች፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በህንድ ላይ ከሩሲያ ድፍድፍ ነዳጅ በመሸመቷ ተጨማሪ ታሪፍ መጣላቸው ይታወሳል፡፡ በቻይና ላይ ግን ይህንን አላደረጉም፡፡
ዋና መቀመጫውን ቤጂንግ ያደረገው የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ከተመሰረተ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሆኖታል፡፡ ቻይና፡ሩሲያ እና ሌሎች አራት የማዕከላዊ እስያ አገራት መስራች አባሎች ናቸው፡፡ ህንድ ይህንን ድርጅት የተቀላቀለችው በ2017 ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ሺ የሻንጋይ የትብብር ድርጅት የልማት ባንክ ማቋቋም ስለሚቻልበት ሁኔታ ማንሳታቸው ተነግሯል፡፡ ቤጂንግ ለአባል አገራቱ የ280 ሚሊዮን ዶላር የነጻ ድጋፍ እንደምታደርግና ለልማት ባንኩ ምስረታ የሚሆን ደግሞ የ10 ቢሊዮን ዩዋን ብድር እንደምትሰጥ ገልጸዋል፡፡
ቤጂንግ ይህንን ጉባኤ ከኒውዴሊህ ጋር ሻክሮ የነበረውን ግንኙነቷን ለማደስም ተጠቅማበታለች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ቻይናና ህንድ በድንበር አከባቢ ግጭት ከገቡ ከ7 ዓመታት በኋላ ነው ወደ ቻይና የገቡት፡፡
በዘንድሮው ጉባኤ ከፑቲንና ሞዲ በተጨማሪ የኢራኑ ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዜሽኪያን፡የቤላሩሱ አሌክስአንድር ሉካንሼንኮን ጨምሮ የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትርም ተገኝተዋል፡፡
ይህ የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ከአለም ጠቅላላው ህዝብ ውስጥ 43 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ የሚይዝ ነው፡፡ ይህም ማለት ከ3.2 ቢሊዮን ህዝብ በላይ ማለት ነው፡፡ በተጨማሪ ከአጠቃላይ የዓለም ጂዲፒ ውስጥም 23 በመቶውን የዚህ ትብብር አባል አገራት እንደሚይዙ ታውቋል፡፡
የሻንጋይ የትብብር ድርጅት የተቋቋመው በ1996 በአምስት አገራት ነው፡፡ ሲቋቋም ይዞ የተነሳው ዓላማም የቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃቱን እንዲሁም የሶቬት ህብረት መፍረሱን ተከትሎ የተፈጠሩ የድንበር ግጭቶችን ለመፍታት በሚል ነበረ፡፡
ህንድ በ2017 ድርጅቱን ስትቀላቀል፤ኢራን ደግሞ በ2023 ቤላሩስ ባለፈው ዓመት ተቀላቅለዋል፡፡ የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ሙሉ አባል የሆኑ አገራት 10 ሲሆኑ፤ሁለት አገራት ደግሞ ታዛቢዎች ናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ቱርክ፡ግብጽን እና ሳውዲን ጨምሮ 14 አገራት ደግሞ የንግግር ተሳታፊዎች ናቸው፡፡ እነዚህ 14 አገራት የትብብር ድርጅቱ ቋሚ አባል ሳይሆኑ ነገር ግን መደበኛ የሆነ ግንኙነት ከትብብር ድርጅቱ ጋር ያላቸው ናቸው፡፡
በስብሰባዎች ላይ መሳተፍ የሚችሉ ሲሆኑ ድምጽ ግን አሰጡም፡፡ የክብር አባል ማለትም ይቻላል፡፡//

