አበረታች ቅመም የአትሌቶቻችን የፓሪስ የኦሎምፒክ ፈተና

‹ኢትዮጵያን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው ሃገራት ተርታ ተመድባለች›

የኃይል ሰጪ ንጥረ ነገሮች ጉዳይ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዘርፍ አነጋጋሪነቱ እጅግ እየጨመረ ነው ። በተለይ ዓለም አቀፉ የጸረ ኃይል ሰጪ ንጥረ ነገር ኩባንያ (WADA) ኢትዮጵያን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው ሃገራት ተርታ መመደቡ የችግሩን ግዝፈት የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ አፋጣን ርምጃ ካልወሰደች ምናልባትም ከፓሪሱ ኦሎምፒክ የመታገድም ስጋት አንዣብቧል ። ለዚህም ይመስላል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፤ የባሕል እና ስፖርት ሚንስትር እንዲሁም የኢትዮጵያ ፀረ–አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በጉዳዩ አሳሳቢነት ላይ ተደጋጋሚ ስብሰባዎችን እያደረጉ ነው ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፤ የችግሩን አሳሳቢነት በመግለጽ የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤትን ጨምሮ 23 ማኅበራት እና ተቋማትን ያሳተፈ ስብሰባ እንዲጠራም ጥያቄ አቅርቦ ነበር ።

አለም አቀፉ የአበረታች ቅመሞች ድርጅት ዋዳ የኢትዮጵያ አትሌቶችን ተከታታይ ምርመራ በማድረግ በአስጊ ደረጃ ኤ ግሬድ ላይ አስቀምጣታል፤ ዋዳ በአትሌቶቹ ላይ የሚያደርገውን የዶፒንግ ምርመራ ከፍተኛ ነጥብ የሚያመጡ ከሆነ ደረጃቸውን ከፍ ያደርገዋል፤ ኢትዮጰያ በተደጋጋሚ ግሬድ ኤ በማግኝተ ከዋዳ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተሰጥተታል፤ አሳሳቢ ደርጃ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቶች እንዳሉ ነው ሁኔታው የሚያሳየው፤

ከዚህ በፊት የኬኒያ አትሌቶቸ አበረታች መድሃኒቶችን በመውስዳቸው ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው አሉ፤ እንደውም ይህንን ሁኔታ እያወቁ ዝም ባሉ የኬኒያ አሰልጣኞች ላይ እርምጃ ሁሉ ተወስዳል፤ ፌዴሬሽኑ የአትሌቶች ማናጀሮችንና አሰልጣኞችን ላይ የነበረው ክትትል አነስተኛ ስለነበር የኬኒያ አትሌቶች አብዛኛዎቹ የዚህ አበረታች መድሃኒተ ሰለባ ሆነው ተግኝተዋል፤ በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ድርጊቶች እየተፈጸሙ መሆኑን እየታየ ነው፤

በቅርቡም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፤ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ አትሌቶች ያሉባቸውን ስጋቶች የተመለክተ አስቸካይ ስብሳባ ተጥርቶ ነበር፤ ስበሳባው ላይ የተገኙ የስራ ሃላፊዎች ንትርክና እጅ መጠቀቆም የበዛበት ስብሰባ መደረጉን ነው በወቅቱ በስብሰባው ላይ የተገኙ ግለሰቦች የተናገሩት፤ እጅ መጠቀቆሙ ሃላፊነትን የመሸሽና ራስን ከተጠያቂነት የማራቅ እንደሆነ ነው የተነገረው፤ ከዚህም በላይ መንግስትን የወከለው ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የፓሪስ ኦሎምፒክ ሃገራዊ አጀንዳ ከመሆኑ አንጻር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በጉዳዩ ላይ እንዲገባና ሁኔታዎችን እንዲያስተካክል ፍላጎት አሳይቶ ነበር፤ ነገር ግን ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ራሱ የመንግስት ተወካይ ሆኖ ሳለ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤትን መጋበዝ መፈለጉ ለአትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ሆነ አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤትን አላሳመነም፤ በስፖርቱ ውስጥ የመንግስትን ጣልቃ ገብነት ያሳያል በሚልም ተቃውሞ ቀርቦበታል፤

የፓሪስ ኦሎምፒክ የተቃረበ ከመምትጣቱ አንጻር ችግሩ ቶሎ ተፈተቶ ወደ ስራ ካልተገባ መንግስታዊ ድጋፍ ያለው የአበረታች ቅመሞች ልምምድ እንዳለ ከታመነ ኢትዮጵያ እንደ ሩሲያ ሁሉ ከኦሎምፒክ ውድድሮቸ ልትታገድ ትችላለች የሚለው ስጋት በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ሰፍናል፤ በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ አትሌቶች አበረታች ቅመሞችን ተጠቅመው ስለመገኘታቸው ቢነገርም የኢትዮጵያ የጸረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ግን የአትሌቶቹን ስም በመደበቅ ችግሩ ከስረ መሰረቱ እንዳይፈታ እያደረገ ነው በሚል እየተወቀሰ ነው፡፡

አለም አቀፉ የጸረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በአለም አቀፍ ደረጃ በምርምራ ዶፒንግ የተገኘባቸውን አትሌቶች ቀን ሰአትና ቦታውን ጭምር በመግለጽ ቢያሳውቅም የኢትዮጵያው የጸረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ግን ስለትሌቶቹ ማንነት ምንም ያለው ነገር የለም፤ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም አትሌቶች ለውድድር ወደ ውጭ ሃገር ሲሄዱ በእርሱ ፈቃድ መሆኑ እየታወቀ ችግር ያለባቸው አትሌቶች ሲኖሩ ለማጣራትና ቁጥጥር ለማድረግ ያለመሞከሩ አስተችቶታል፤ ሌሎች አትሌቶች እንዲማሩበት ለማድረግ በሚያስችል መልኩ ቶሎ የእርምት እርምጃ አለመወሰዱም የችግሩን ስፋት ማሳያ ተድርጎ ተወስዳል፤ ለአትሌቶቹ ይሰጥ የነበረው ትምህርትና ስልጠናም መቀዛቅዙ ሌላው ችግር ሆናል፤

ያም ሆኖ ግን በስተመጨረሻ ጉዳዩ ሃገራዊ መሆኑን በመረዳት አንድ ኮሚቴ በማቀቀም ከፓሪስ ኦሎምፒክ በፊት በኢትዮጵያ አትሌቶች ላይ የሚነሳውን የጸረ አበረታች ቅመሞች ችግር ለመፍታት ከስምምነት ላይ ተድርሳል፤ ይሁን እንጂ ኮሚቴው ቢቀቀምም በፋይናንስ ችግር ሳቢያ ላለፉት ሁለት ወራት ስራውን መጀመር እንዳልቻል ታውቀል፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ ካልሰሩ በስተቀር የፓሪስ ኦሎምፒክ እየተቃረበ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ የቀደመ ስማን ይዛ ለመቅረብ ያስቸግራታል የሚል አስተያየቶ እየተደመጡ ነው፤ ለኦሎምፒክ ቡድኑ የሚያስፈልገው በጀት አእስካሁን ድረስ ስጸድቆ የገቢ ማሰባሰቢያ ፐሮግራሞች አለምካሄዳቸው ሲታሰብ ደግሞ ስርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ የመሆን አዝማሚያ ይታያል፤

ቀደም ባሉት አመታት የኦሎምፒክ ውድድር ሲቃረብ በኢትዮጵያ ኦልፕምፒክ ኮሚቴና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፊሬሬሽን መሃክል የሚኖረው ውዝግብ የውድድሩ ባልቤት አእኔ ነኝ አእኔ ነኝ በሚል ነበር፤ አሁን ደግሞ ይህ ውዝግብ መልኩን ለውጦ ለአትሌቶቻችን ስጸረ አበረታች ቅምመሞች መጠቅም ሃላፊው ማነው ብወደሚል የተቀየረ ይመስላል፤ይራል፤ ስብሰባና የኝዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች አስፈላጊ ቢሆኑም ከጊዜ እጥረት አንጻር ቶሎ ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ካልተገባ የኢትዮጵያ የፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳትፎ ከተሳትፎ ያልዘለል ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አለ፤ ባለፉት ተከታታይ የኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ በተለያየ ምክንያት ኢትዮጵያ ከሁለት ወርቅ በላይ ልታመጣ አለመቻላ በበቂ ሁኔታ ባለመገመገሙ ዘንድሮም ተመሳሳይ ውጤት ለመድገም ወደ ፓሪስ ሊኬድ ይችላለ የሚል ስጋት አለ፤

ከአትሊቶቻችን ጀርባ ሆነው አበረታች ቅመሞችን አእነዲጠቀሙ የሚያደርጉ የህግረ ውስጥም ይሁን የውጭ ሃገር አሰልጣኞችንና ማናጀሮችን ተክታትሎና መርምሮ አእርምጃ ከውዲሁ ካልተወሰደ በአበረታች ቅመሞች ስማ ተነስቶ የማያወቅው ሃገራችን ከኦሎመፒክ መንደር አእስከመታገድ የሚያደርስ ችግር ላይ ለትወድቅ ስለመተችል ተኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው

በሌላ በኩል በፓሪስ የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ቅድመ ልምምዳቸውን በፈረንሳይ ሊያደርጉ የሚችሉበት የመግባቢያ ሥምምነት መፈረሙ ኢትዮጵያ ለፓሪስ ኦሎምፒክ ተኩረት ከወዲሁ መስጠትን ያሳያል ተብላል፤ ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ደራርቱ ቱሉ እና የአንቶኒ ከተማ ከንቲባ ዦን ኢቭ ሴኖ ናቸው።

በሚቀጥለው ዓመት በፓሪስ በሚካሔደው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ቅድመ ልምምዳቸውን በፈረንሳይ ሊያደርጉ የሚችሉበት የመግባቢያ ሥምምነት ተፈረመ። ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ደራርቱ ቱሉ እና የአንቶኒ ከተማ ከንቲባ ዦን ኢቭ ሴኖ ናቸው።

ቅድመ ሥምምነቱ “ከታመነበት” በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አንቶኒ ወደ ተባለችው ከተማ ቀድመው በመጓዝ ልምምድ እንንደሚሰሩ ደራርቱ ቱሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

አንቶኒ ከፓሪስ በስተደቡብ በ12 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የምትገኝ ነች። የፓሪስ ኦሎምፒክ ከሐምሌ 19 እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2016 በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ይካሄዳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe